በአሁኑ ሰአት የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከአምስት ቢሊዮን በላይ አልፏል
በአሁኑ ሰአት የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከአምስት ቢሊዮን በላይ አልፏል።
ባለፈው ረቡዕ እለት የታተመ ሪፖርት እንደሚያመለክተው ከሆነ በአሁኑ ወቅት ማህበራዊ ሚዲያን እየተጠቀሙ ያሉ ሰዎች ቁጥር ወደ አምስት ቢሊዮን ከፍ ማለቱን ይፋ አድርጓል።
እንደሪፖርቱ ይህ ቁጥር የአለምን ህዝብ 62.3 በመቶ ይሆናል።
ሪፖርቱን ያወጡት የሞኒተሪንግ ኩባንያው 'መልቲወተር' እና 'ዊአር ሶሺያል' ሚዲያ ኤጀንሲ እንደገለጹት ባለፈው አመት የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጥር 5.6 በመቶ አድጓል፤ ይህም የአለም ህዝብ ቁጥር ካደገበት 0.9 በመቶ ይበልጣል።
ኤኤፍፒ እንደዘገበው የሜታው ፌስቡክ 2.19 ቢሊዮን ተከታዮች አንደኛ ደረጃ ይዟል።
ሌላኛው በሜታ ስር የሚተዳደረው ኢንስታግራም ደግሞ 1.65 ቢሊዮን ተከታዮች በማፍራት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ባለቤትነቱ የቻይናው ባይቲዳንስ የሆነው የአጭር ቪዲዮ ማጋሪያ የሆነው ቲክቶክ በ1.56 ቢሊዮን ተከታዮች ሶስተኛነት ይከተላል።
ሪፖርቱ አንድ ሰው በተለያየ ማንነት ከአንድ በላይ አካውንት ሊኖረው ስለሚችል መረጃው ውስንነት ሊኖረው ይችላል ብሏል።