ጠላፊዎቹ በዓመት 300 ሺህ ሰዎችን ኢላማ በማድረግ 60 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እያገኙ እንደሆነ ተገልጿል
ከፍተኛ የመረጃ መንታፊዎች የሚገኙባቸው ሀገራት
ሜታ ኩባንያ ከሰሞኑ በስሩ ባሉ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ተጠቃሚዎች መስለው ገንዘብ እና መረጃ መንታፊዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡
በተለይም ፌስቡክን ተጠቅመው አድብተው የተጠቃሚዎችን ገንዘብ ሲመትፉ ነበር ያላቸውን ከ2 ሚሊዮን በላይ አካውንቶችን እንደዘጋ ገልጿል፡፡
እንደ አሜሪካ ሰላም ኢንስቲትዩት ሪፖርት ከሆነ በዓመት 300 ሺህ የዓለማችን ዜጎች ለነዚህ መረጃ መንታፊዎች ተገደው ገንዘባቸውን ያስተላልፋሉ፡፡
እነዚህ መረጃ መንታፊዎች በየዓመቱ 60 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እያገኙ ነው የተባለ ሲሆን መንታፊዎቹ አሳሳች ማንነት ስለሚጠቀሙ ተጠያቂ ለማድረግ አስቸጋሪ ነውም ተብሏል፡፡
ማይናማር፣ላኦስ፣ ካምቦዲያ፣ ፊሊፒንስ እና ታይላንድ ከፍተኛ የመረጃ መንታፊዎች ማዕከላት ከሆኑ የዓለማችን ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡