ዴይሲ… አጭበርባሪዎችን ለይቶ የሚያጠምደው አዲሱ ቴክኖሎጂ
የብሪታንያው ቴክኖሎጂ ኩባንያ አጭበርባሪዎችን አዘናግቶ የሚያጋልጥ ኤአይ ምርት ይፋ አድርገዋል
አጭበርባሪዎች በአሜሪካ በየዓመቱ 10 ቢሊዮን ዶላር ይመዘብራሉ
ዴይሲ አጭበርባሪዎችን ለይቶ የሚያጠምደው አዲሱ ቴክኖሎጂ
ቴክኖሎጂዎች በየጊዜው እየዘመኑ እና የሰው ልጆችን አኗኗር እያቀለሉ መጥተዋል፡፡
በዚያው ልክ ደግሞ ይህ ቴክኖሎጂ ለአጭበርባሪዎች በቀላሉ መንገዶችን የፈጠሩ ሲሆን ብዙዎች እንደቀልድ ገንዘባቸውን እና መረጃዎቻቸውን ተመዝብረዋል፡፡
በአሜሪካ እና ብሪታንያ በተካሄደ ጥናት ከሶስት ሰዎች አንዱ ለድጅታል አጭበርባሪዎች የተጋለጡ ሲሆን በአማካኝ አንድ ሰው 1 ሺህ 600 ዶላር ገንዘባቸውን ተመዝብረዋል፡፡
የብሪታንያው ቨርጂን ሚዲያ 02 ኩባንያ አጭበርባሪዎችን ለይቶ የሚይዝ ቴክኖሎጂ ይፋ አድርጓል፡፡
እንደ ቢዝነስ ኢንሳይደር ዘገባ ከሆነ ይህ ቴክኖሎጂ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም የለማ ሲሆን ባጭሩ ዴይሲ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
ለዓመታት ያለ ስራ ከ16 ተቋማት ደመወዝ ስትቀበል የነበረችው አጭበርባሪ ተያዘች
ዴይሲ አጭበርባሪዎች የሰዎችን መረጃ ወይም ገንዘብ ለመውሰድ ወደ እጅ ስልኮች መግባት የሚያስችላቸውን ጥረት ሲያደርጉ እያዘናጋ ጊዜያቸውን በመብላት እና የማዘናጋት ስራ የሚሰራ ቴክኖሎጂ ነው፡፡
ቴክኖሎጂው አጭበርባሪዎችን ከማጋለጥ አልፎ ባለ ስልኮች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የሚያሳስብ ነውም ተብሏል፡፡
አጭበርባሪዎች በአሜሪካ በየዓመቱ 10 ቢሊዮን ዶላር የሚመዘብሩ ሲሆን የሀገሪቱ መንግስት ዜጎችን እንዲጠነቀቁ በየዓመቱ በማሳሰብ ላይ ነው፡፡