ኖቤል በተለያዩ ዘርፎች ልዩ አበርክቶ ላበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት የሚሰጥ ሽልማት ነው
የኖቤል ሽልማት በየዓመቱ በተለያዩ የሙያ መስኮች አዲስ አበርክቶ ላደረጉ ግለሰቦች እና ተቋማት ይሰጣል።
ወርልድ ኢንዴክስ የኖቤል ሽልማት ኢንስቲትዩትን መረጃ ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ጀርመን እስከ ሶስተኛ ድረስ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በፈረንጆቹ 2018 የሰላም ኖቤል ሽልማትን ማሸነፏ ይታወሳል።
ዋና መቀመጫውን በስዊድን ያደረገው የዚህን ተቋም ሽልማት ደጋግመው የወሰዱ የዓለማችን ሀገራት ዝርዝር እና የወሰዷቸው ሽልማዮች ብዛት የሚከተለውን ይመስላሉ።