የኖቤል ሽልማት አሸናፊው የ10 ዓመት እስራት ተፈረደባቸው
አሌስ ቢያሊያትስኪ ተቃውሞዎችን በገንዘብ በመደገፍና በታክስ ማጭበርበር ተከሰው ነው ጥፋተኛ የተባሉት
በ2020 ምርጫን ተከትሎ በተካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ አያሌ ቤላሩሳዊያን ተብሏል
የቤላሩስ ፍርድ ቤት የኖቤል የሰላም ተሸላሚውን አሌስ ቢያሊያትስኪን የ10 ዓመት እስራት ፈርዶበታል።
ብይኑ በምዕራባውያን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አጥብቆ ሊወገዝ ይችላል ተብሏል።
አሌስ ቢያሊያትስኪ በፈረንጆች 2020 ቤላሩስ ውስጥ በተነሳው ብጥብጥ ለተቃዋሚዎች የህግ እና የገንዘብ እርዳታ የሰጠው የቪያና የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና መስራች ናቸው።
ቢያሊያስኪ ተቃውሞዎችን በገንዘብ በመደገፍና በታክስ ማጭበርበር ተከሰው ነው ጥፋተኛ የተባሉት።
ክሱ ፖለቲካዊ መሆኑን በፍርድ ቤት በነበራቸው ክርክር ሲናገሩ ነበር ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
ባያሊያትስኪ ህይወት ዘመናቸውን ለዲሞክራሲ እና ለሰብዓዊ መብት ሲታገሉ ነበር የተባለ ሲሆን፤ በ2022 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል
የመብት ተሟጋች ቡድኖች በቤላሩስ ውስጥ ወደ አንድ ሽህ 500 የሚጠጉ የፖለቲካ እስረኞች እንዳሉ የሚናገሩት ሲሆን፤ በ2020 የተካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ ብዙዎች ታስረዋል።
አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ምርጫውን "አሸነፍኩ" ማለታቸውን ተከትሎ በቤላሩስ ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀስቅሷል።
በምዕራቡ ዓለም እና የቤላሩስ ተቃዋሚዎች ግን ምርጫው ተጭበርብሯል ብለዋል።