የኖቤል ተሸላሚው ሩሲያዊ ጋዜጠኛ ሜዳሊያውን በ103 ሚሊየን ዶላር ለጨረታ አቀረበ
ጋዜጠኛ ዲመትሪ ሙራቶቭ ዩክሬናውያንን ለመርዳት ሲል ሜዳሊያውን ለጨረታ ያቀረበው
የሜዳሊያው ሽያጭ እየተካሄደ ያለው በኒውዮርክ መሆኑም ተገልጿል
የኖቤል ተሸላሚው ሩሲያዊ ጋዜጠኛና የኖቫያ ጋዜጣ ዋና አርታዒ ዲመትሪ ሙራቶቭ ሜዳሊያውን በ103.5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ለጨረታ አቀረበ።
ዲመትሪ ሙራቶቭ፡ ከሽያጩ የሚያገኘው ገንዘብ በዩክሬን እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት ለተሰደዱ ዩክሬናውያን በተለይም ህጻናት ድጋፍ እንደሚውል አስታውቋል።
የሜዳሊያው ሽያጭ እየተካሄደ ያለው በኒውዮርክ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ሙራቶቭ በዋና አርታዒነት የሚሰራበት ኖቫያ ጋዜጣ ሩስያ በዩክሬን ላይ የጀመረቸውን ወታደራዊ ዘመቻ ተከትሎ ባሰለፍነው ወርሃ መጋቢት ስራውን አቁሟል፡፡
ጋዜጣው የተዘጋው የክረምሊን ሰዎች በዩክሬን ላይ እየተካሄደ ያለው “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” እንጅ “ጦርነት” ብሎ መግለጽ ከባድ ቅጣት ያስከትላል የሚል ትእዛዝ ማውረዱን ተከትሎ ነው፡፡
ሙራቶቭ እንደፈረንጆቹ 1993 የሶቭየት ህብረት ካምፕ መፈረካከስን ተከትሎ የኖቫያ ጋዜጣ ከመሰረቱ ጋዜጠኞች መካከል አንዱ ነው፡፡
ጋዜጠኛ ሙራቶቭ በፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አስተዳደር ላይ የሰላ ትችት በመሰንዘር ከሚታወቁት ጋዜጠኞች አንዱ መሆኑም ይታወቃል፡፡
በዚህም የክሬምሊን ሰዎች አላሰራ ስላሉት ወደ አውሮፓ ምድር ተሰዶ ለመኖር የተገደደ ጋዜጠኞ ነው፡፡
ጋዜጠውኛው የፊሊፒንስ እና አሜሪካዊ ዜግነት ካላት ጋዜጠኛ ማሪያ ሪሳ ጋር በመሆን ለጋዜጠኝነት ባበረከቱት አስተዋጽኦ የ2021 የሰላም ኖቤል ሽልማትን ማሸነፉም አይዘነጋም፡፡