ጋዜጠኛ ዲሚትሪ ሙራቶቭ ሜዳሊያውን የሚሸጠው የዩክሬን ስደተኞችን ለመርዳት ነው ተብሏል
ሩሲያዊው የሰላም ኖቤል አሸናፊ ጋዜጠኛ ስደተኞችን ለመርዳት ሲል ሜዳሊያውን ሊሸጥ መሆኑን ገለጸ፡፡
ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ከሩሲያ ጋር ጦርነት ከጀመሩ አራት ወራት ሊሞላው ጥቂት ቀናት ብቻ ይቀራል፡፡
በነዚህ ቀናት ውስጥ 15 ሚሊዮን ዩክሬናዊያን ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው በጎረቤት ሀገራት እና በሀገር ውስጥ በተዘጋጁ መጠለያ ጣቢያዎች ሰፍረው ይገኛሉ፡፡
ከአንድ ዓመት በፊት ሀሳብን በነጻነት ከመግለጽ አንጻር ለዲሞክራሲ መስፈን ባበረከቱት አስተዋጽኦ የዓለም ሰላም ኖቤል ሽልማት የተቀዳጀው ሩሲያዊው ጋዜጠኛ ዲሜትሪ ሙራቶቭ ስደተኞችን ለመርዳት በሚል ሜዳሊያውን ሊሸጥ መሆኑን ተናግሯል፡፡
“አሜሪካ ከቀዝቃዛው ጦርነት በኋላ ራሷን እንደ ፈጣሪ መልዕከተኛ አድርጋ ነው የምታስበው” - ፑቲን
የቀድሞው የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ እና የኖቫያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ሙራቶቭ ዩክሬናዊያን እየደረሰባቸው ባለው ጉዳት ማዘኑን ገልጿል፡፡
ጋዜጠኛ ሙራቶቭ በፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አስተዳደር ላይ የሰላ ትችት በመሰንዘር የሚታወቅ ሲሆን ከሞስኮ ተሰዶ በአውሮፓ ሀገራት ነው የሚኖረው፡፡
ጋዜጠውኛ የፊሊፒንስ እና አሜሪካዊ ዜግነት ካላት ጋዜጠኛ ማሪያ ሪሳ ጋር በመሆን ለጋዜጠኝነት ባበረከቱት አስተዋጽኦ የ2021 የሰላም ኖቤል ሽልማትን አሸንፈዋል፡፡
ረጅም ጊዜ ለዩክሬናዊያን ስደተኞች ምን ማድረግ እንደምችል ሳስብ ነበር የሚለው ጋዜጠኛ ሙራቶቭ በእጄ ላይ ያለውን የሰላም ኖቤል ሜዳሊያ ሸጬ የተቸገሩ ዜጎችን እረዳለሁ ማለቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ሜዳሊያውን የዓለም ስደተኞች ቀን በሚከበርበት ሰኔ 20 ቀን ለሽያጭ እንደሚውል የገለጸው ጋዜጠኛው ሁሉም ሩሲያውያን ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር እንዳልሆኑ ዓለም ሊያውቀው ይገባልም ብሏል፡፡