ከፍተኛ ማዕቀብ የተጣለባቸው ሀገራት
ሩሲያ ሉሀንስክ እና ዶምባሰን ነጻ ግዛት ናቸው ብላ ካወጀች በኋላ የተጣለባት ማዕቀብ ቁጥር በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በስድስት እጥፍ ጨምሯል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ዘመቻ ከጀመረች በኋላ ከፍተኛ ማዕቀብ ከተጣለባቸው ሀገራት ውስጥ ቀዳሚ ሆናለች
ከፍተኛ ማዕቀብ የተጣለባቸው ሀገራት
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ዘመቻ ከጀመረች በኋላ ከፍተኛ ማዕቀብ ከተጣለባቸው ሀገራት ውስጥ ቀዳሚ ሆናለች።
ሩሲያ በፈረንጆቹ የካቲት 2022 በዩክሬን ውስጥ ያሉትን ሁለት ግዛቶች ማለትም ሉሀንስክ እና ዶምባሰን ነጻ ግዛት ናቸው ብላ ካወጀች በኋላ የተጣለባት ማዕቀብ ቁጥር በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በስድስት እጥፍ ጨምሯል።
የስታቲስታ መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ ፑቲን ዩክሬንን መውረራቸዉ፣ ሩሲያ በምዕራብ እስያ የአሜሪካ ቀንደኛ ጠላት እንድትሆን አድርጓታል።
ፑቲን በዩክሬን ላይ ዘመቻ ከመክፈታቸው በፊት ኢራን በአሜሪካ፣ በአውሮፖ ህብረት፣ በካናዳ፣ በእስራኤል እና በአውስትራሊያ በተጣሉ 3616 ማዕቀቦች በታሪክ ቀዳሚ ተጠቂ ነበረች።
በእነዚህ ሀገራት እና በኢራን መካከል የነበረው ግንኙነት ከፍተኛ መሻከር ያጋጠመው ከኢራን ኑክሌር የጦር መሳሪያ ማበልጸግ ጋር በተያያዘ ምክንያት ነበር።
በእርስ በእርስ ጦርነት የታመሰችው ሶሪያ ደግሞ የማዕቀብ ተጠቂ በመሆን በሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
አሜሪካ፣ ካናዳ፣ስዊዘርላንድ እና ዩናይትድ ኪንግደም(ዩክ) በተከታታይ 3551፣2765፣2225፣1749 ማዕቀቦችን በመጣል ቀዳሚ ናቸው።
ማዕቀቦቹ ኢላማ ያደረጉት በ11462 ሩሲያውያን ግለሰቦች እና ድርጅቶች ላይ ነው ተብሏል።