የአቶ ዮሐንስ ቧያለው በአማራ ክልል እንዲሁም በፌደራል ደረጃ በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች ላይ ሲሰሩ ቆይተዋል
የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል የነበሩት የአቶ ዮሐንስ ቧያለው ያለመከሰስ መብት ተነሳ።
የአማራ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማድረግ ላይ ይገኛል።
ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎው ክልሉ ምክር ቤት አባል የነበሩትን የአቶ ዮሐንስ ቧያለውን ያለመከሰስ መብት ማንሳቱን የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።
የአቶ ዮሐንስ ቧያለው በአማራ ክልል እንዲሁም በፌደራል ደረጃ በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች ላይ ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወቃል።
በያዝነው ሳምንት ጨፌ ኦሮሚያ የክልሉ ምር ቤት አባል የነበሩትን አቶ ታየ ደንደዓን ያለመከሰስ መብት ማንሳቱም ይታሳወሳል።
የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል በወቅቱ ባወጣው መግለጫም አቶ ታየ ደንደዓ “በተለያዩ አካባቢዎች በንፁሃን ዜጎች ላይ ሲፈፀሙ በነበሩ የሽብር ተግባራት በተለይም ደግሞ ከእገታ ጋር በተያያዘ እጁ እንዳለበት ተደርሶበታል” ብሏል።
በባህርዳር ከተማ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲን ወክለው ተወዳድረው የተመረጡት እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ጥር 22 ቀን 2016 ዓ .ም እንደታሰሩ ቤተሰባቸው መናገራቸው አይዘነጋም።
በክልሉ የታወጀው የአስቸኳይ አዋጅ ምክንያት በማድረግ ሌላኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል ከስድስት ወራት በፊት መታሰራቸው ይታወሳል።