ልዩልዩ
በ2024 ሙዚቃቸው በብዛት የተደመጠላቸው አርቲስቶች እነ ማን ናቸው?
ቴይለር ስዊፍት፣ ዘ ዊክኢንድ እና ድሬክ እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት ውስጥ ሙዚቃቸው በብዛት ከተደመጠላቸው አርቲስቶች መካከል ዋነኞቹ ናቸው

የሳብሪና ካርፔንተር “ኢስፕሬሶ” የተሰኘው ሙዚቃ በዓመቱ በብዛት የተደመጠው ሙዚቃ ተብሏል
በ2024 ሙዚቃቸው በብዛት የተደመጠላቸው አርቲስቶች እነ ማን ናቸው?
የፈረንጆቹ 2024 ዓመት ሊጠናቀቅ ሶስት ሳምንታት ብቻ የቀሩት ሲሆን በዓመቱ የነበሩ ልዩ ክስተቶች እየወጡ ይገኛሉ፡፡
ከነዚህ መካከል ሙዚቃ አንዱ ሲሆን በዓመቱ ውስጥ በብዛት የተደመጠላቸው አርቲስቶች ሪፖርት ይፋ ሆኗል፡፡
በዓለማችን ካሉ ዋነኛ የሙዚቃ ማሰራጫዎች መካከል አንዱ የሆነው ስፖቲፋይ ሪፖርት ከሆነ አሜሪካዊቷ ቴይለር ስዊፍት ቀዳሚዋ ሆናለች፡፡
በስፖቲፋይ የሙዚቃ ማጫወቻ ላይ ሙዚቃቸው በብዛት ከተደመጠላቸው አርቲስቶች መካከል ቀዳሚዋ አሜሪካዊ፣ ብሪታንያ እና የካናዳ አርቲስቶች ቀዳሚ ሆነዋል፡፡
የዘር ሀረጉ ከኢትዮጵያ የሚመዘዘው ዘ ዊክኢንድ ደግሞ ሁለተኛው ሲባል ባድ በኒ እና ድሬክም ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡
“ኢስፕሬሶ” የተሰኘው የሳብሪና ካርፔንተር ሙዚቃ በዓመቱ ውስጥ በብዛት የተደመጠው ሙዚቃ ሲባል “ቢውቲፉል” የተሰኘው የቤንሰን ቡን ሙዚቃም ሁለተኛው ተወዳጅ ሙዚቃ ተብሏል፡፡