የሻይ ጤና በረከቶች ምን ምን ናቸው?
ሻይ በዓለማችን ከውሀ ቀጥሎ በሰው ልጆች የሚወሰድ ምርት ይወሰዳል
ቻይና፣ሕንድ እና ኬንያ የዓለማችን ቀዳሚ ሻይ አምራች ሀገራት ናቸው
የሻይ ጤና በረከቶች ምን ምን ናቸው?
በየዕለቱ ከማዕዳችን የማይጠፋው ሻይ ከውሀ በመቀጠል የሰው ልጆች አብዝተው ይጠጣል።
በፈረንጆቹ ግንቦት 21 በየ ዓመቱ የሻይ ቀን ተብሎ የሚከበር ሲሆን ዕለቱም ስለ ሻይ ጥቅሞች የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችን በመስራት ይከበራል።
በቻይናዊያን እንደተጀመረ የሚገለጸው ሻይ አሁን ላይ ያለው የኢኮኖሚ ድርሻ ከ56 ቢሊዮን ዶላር አልፏል።
ይህ ኢንዱስትሪ በ2030 በዓለም ኢኮኖሚ ላይ የሚኖረው ድርሻ ወደ 95 ቢሊዮን ዶላር ከፍ እንደሚል ዓለም አቀፉ የምግብ ድርጅት ወይም ፋኦ ሪፖርት ያስረዳል።
አሁን ላይ በዓመት የሚመረተው የሻይ መጠን ከ6 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ቶን የደረሰ ሲሆን የተጠቃሚዎች ቁጥር በዓመት ከ3 በመቶ በላይ እያደገ ነውም ተብሏል።
ቻይና የዓለማችን የሻይ ፍላጎት 47 በመቶ የምታመርት ሲሆን ሕንድ እና ኮንያም በቅደም ተከተል ሁለተኛ እና ሶስተኛ የሻይ አምራች ሀገራት ናቸው።
ሻይ ካፊን የተሰኘው አነቃቂ ንጥረ ነገር የያዘ በመሆኑ ሰዎች ድካም እንዳይሰማቸው፣ ድርቀትን ለመከላከል፣ የሰውነት በሽታ የመከላከል አቅምን ማጎልበት፣ ድብርትን እና ትኩረት ማጣትን እንደሚከላከል የጤና ባለሙያቆች ይመክራሉ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሻይ ምርት በአየር ንብረት ለውጥ እየተጎዳ ያለ ኢንቨስትመንት የሆነ ሲሆን ጉዳቱ እንዲቀንስ ካልተደረገ የሻይብዋጋ መናር፣ የሻይ አምራች ገበሬዎች እና ኩባንያዎች ከስራ ውጪ የመሆን እድል ተጋርጦባቸዋል ተብሏል።