6.6 ቢሊየን ዶላር ዋጋ የወጣለት የስፔኑ ሪያል ማድሪድ ቀዳሚ ሆኗል
የቢሊዮን ዶላሮች ገበያ የሚያንቀሳቅሰው እግር ኳስ ተወዳጅነቱ አለም አቀፋዊ ነው፡፡ ቡድኖች በተጫዋች ሽያጭ ፣ በስፖንሰር፣ የቴሌቪዥን ውል፣ በማሊያ እና በትኬት ሽያጭ በአመት ከፍተኛ ገንዘብ ያገኛሉ፡፡
ከዚህ የአጠቃላይ የቡድኖቹ አመታዊ ገቢ እንዲሁም ከደጋፊዎቻቸው ቁጥር በመነሳት ቡድኖቹ ምን ያክል እንደሚያወጡ በአመት ዋጋ ይተመንላቸዋል፡፡
በ2024 የስፔኑ ሪያል ማድሪድ ቀዳሚውን ስፍራ የያዘ ክለብ ሆኗል የቡድኑ አጠቃላይ ዋጋም 6.6 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን በ2023/24 የውድድር አመት 844 ሚሊየን ዶላር ትርፍ አግኝቷል፡፡
የእንግሊዙ ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ ባለፉት አመታት ጠንከራ የማይባል አቋም ቢያሳይም ወጋውን ግን አሁንም አልቀነሰውም 5.6 ቢሊየን ዶላር ዋጋ የወጣለት ክለቡ ከእንግሊዝ ቡድኖች ቀዳሚው ነው፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ ውድ የእግርኳስ ቡድኖች ተብለው የተለዩ 50 ክለቦች አጠቃላይ ዋጋ 79.6 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ የወጣላቸው ሲሆን በአመት የሚያገኙት የተጣራ ትርፍ በመቶ ሚሊዮን ዶላሮች የሚሰላ ነው፡፡