በ2024 በብዛት የተጎበኙ 10 የዓለማችን ሀገራት
የኦሎምፒክ አዘጋጇ ፈረንሳይ 90 ሚሊዮን ገደማ ጎብኚዎችን ስባለች
ጎብኚዎችን አትምጡብኝ በማለት የምትታወቀው ስፔን በ84 ሚሊዮን ሰዎች ተጎብኝታለች
በ2024 በብዛት የተጎበኙ 10 የዓለማችን ሀገራት
ዓለም አቀፉ ቱሪዝም ድርጅት ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት መሰረት ፈረንሳይ በ2024 ዓመት ውስጥ ብቻ በ89 ሚሊዮን ጎብኚዎች ተጎብኝታለች፡፡
ሀገሪቱ የኦሎምፒክ ውድድር አዘጋጅ ሀገር መሆኗ ጎብኚዎችን በመሳብ የዓለማችን ቀዳሚዋ ሀገር እንድትሆን አስችሏታል፡፡
ይሁንና ፈረንሳይን የጎበኙ ጎብኚዎች የጣሰበውን ያህል ወጪ አላወጡም የተባለ ሲሆን ይህም የታሰበውን ያህል ገቢ እንዳታገኝ አድርጓታል ተብሏል፡፡
84 ሚሊዮን ጎብኚዎችን በመሳብ ከፈረንሳይ በመቀጠል ሁለተኛዋ ሀገር የሆነችው ደግሞ ስፔን ናት፡፡
ስፔናዊያን በጎብኚዎች ተጥለቀለቅን በሚል የጎብኚዎች ቁጥር እንዲቀንሱ ዜጎቿ በሰላማዊ ሰልፍ ሳይቀር ጠይቀዋል፡፡
አሜሪካ 79 ሚሊዮን እንዲሁም ቻይና ደግሞ በ66 ሚሊዮን ዜጎች በመጎብኘት ሶተኛ እና አራተኛዎቹ ሀገራ ተብለዋል፡፡