በኢኳዶር "ዋና ተፈላጊ" ወንጀለኛ ከእስር ቤት ጠፋ
ማሲያስ የእፅ ዝውውርን እና ግድያን ጨምሮ በተመሰረተበት በርካታ ክሶች በ2011 ለ31 አመታት ተፈርዶበት ነበር
ፖሊስ አዛዡ ጀነራል ጦሩ በጉያቁሊ እስርቤት ከነበሩት ወንጀለኞች ውስጥ አንዱ መጥፋቱን አረጋግጠዋል
በኢኳዶር "ዋና ተፈላጊ" ወንጀለኛ ከእስር ቤት ጠፋ
በኢኳዶር የሎስ ቾነሮስ የወንጀል ቡድን መሪ እና ዋና ተፈላጊ የሆነው እስረኛ ታስሮ ከነበረበት እስርቤት ማምለጡን ባለስልጣናት ተናገሩ።
የሀገሪቱ ፖሊስ አዛዥ ጀነራል ሴዛር ዛፖታ እንደተናገሩት ጦሩ በጉያቁሊ እስርቤት ከነበሩት ወንጀለኞች ውስጥ አንዱ መጥፋቱን አረጋግጠዋል።
ዛፖታ ጠፋ የተባለውን እስረኛ ስም ባይጠቅሱም፣ የአቃቤ ህግ ቢሮ ግን የሎስ ቾነሮስ ቡድን መሪ አዶልፎ ማሲያስ እንዴት እንደጠፋ ምርመራ ይካሄዳል ብሏል።
ማሲያስ የእፅ ዝውውርን እና ግድያን ጨምሮ በተመሰረተበት በርካታ ክሶች በ2011 ለ31 አመታት ተፈርዶበት ነበር።
የሀገሪቱ ባለስልጣናት ሎስ ቾነሮስን ግድያ፣ እፅ ዝውውር እና ሌሎች ወንጀሎችን በመፈጸም ይከሱታል።
በኢኳዶር እስርቤቶች ተቃናቃኝ የወንጀል ቡድኖች ብዙ ጊዜ የሚደባደቡ ሲሆን ከ2021 ወዲህ 400 አስረኞች ሞተዋል።