ማውሪታኒያ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሆነች
ፕሬዝደንት ኦውልድ ጋዞአኒ ዛሬ የተመረጡት የህብረቱ ስራ አስፈጻሚ ምክርቤት ባለፈው ረብዕ ባካሄደው ጉባኤ እንዲመረጡ ይሁንታ ከሰጣቸው በኋላ ነው ተብሏል
የማውሪታኒያ ፕሬዝደንት መሀመድ ኦዉልድ ጋዞአኒ ከወቅቱ የህብረቱ ሊቀመንበር ከኮሞሮሱ ፕሬዝደንት አዛሊ አሶውማኒ ስልጣን ተረክበዋል
ማውሪታኒያ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሆነች።
ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ማውሪታኒያ በ2024 የአፍሪካ ህብረትን በሊቀመንበርነት እንድትመራ አዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው የህብረቱ 37 የመሪዎች ጉባኤ ላይ ተመርጣለች።
የማውሪታኒያ ፕሬዝደንት መሀመድ ኦዉልድ ጋዞኒ ከወቅቱ የህብረቱ ሊቀመንበር ከኮሞሮሱ ፕሬዝደንት አዛሊ አሶውማኒ ስልጣን ተረክበዋል።
ፕሬዝደንት ኦውልድ ዛሬ የተመረጡት የህብረቱ ስራ አስፈጻሚ ምክርቤት ባለፈው ረብዕ ባካሄደው ጉባኤ እንዲመረጡ ይሁንታ ከሰጣቸው በኋላ ነው ተብሏል።
በጉባኤው በርካታ የህብረቱ አባል ሀገራት መሪዎች እና የአለም አቀፍ የልማት ድርጅቶች ተወካዮች እየተሳተፉበት ይገኛሉ።
የዘንድሮው የመሪዎች ጉባኤ በትምህርት ልማት ላይ ትኩረት ማድረጉ ተገልጿል።
በጉባኤው ላይ እንግድነት የተገኙት የብሪክስ መስራች የሆኑት የብራዚሉ ፕሬዝደንት ሉላ ዳ ሲልቫ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት በቡድን 20 ሀገራት ውስጥ በአባልነት ሊካተቱ እንደሚገባ ተናግረዋል።
ፕሬዝደንት ሉላ ያለአፍሪካ ተሳትፎ ዓለም ምንም ነች በማለት ነው የአፍሪካን ተሳትፎ ወሳኝነት የተናገሩት።
ለሁለት ቀናት የሚቆየው የመሪዎች ጉባኤ በነገው እለት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።