የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ
በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ሙሳ ፋኪ መሀመት አስታውቀዋል
አዲሱ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ አዲስ አበባ ይገኛሉ
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት ከአዲሱ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር መወያየታቸውን አስታወቁ።
አዲሱ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ እና የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ረዳት ጸሃፊ ሞሊ ፊ ካሳለፍነው ሰኞ ጀምሮ በሳዑዲ አረቢያን፣ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ መሆኑ ይታወቃል።
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ እና የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ረዳት ጸሃፊ ሞሊ ፊ የጉብኝታቸው አካል ወደ ሆነችው ኢትዮጵያም ገብተዋል።
በአዲስ አበባ ቆታቸውም ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው ታውቋል።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት በትዊተር ገጻቸው እንዳሳወቁት፤ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ እና የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ረዳት ጸሃፊ ሞሊ ፊን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
በቆይታውም በተለያዩ የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አስታውቀወዋል።
ዴቪድ ሳተርፊልድ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ከሌሎች የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር የተወያዩትን አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማንን ተክተው በቅርቡ በአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛነት መሾማቸው ይታወሳል።
በተለያዩ በተለይም በእርስበርስ ጦርነትና እሰጣገባ ውስጥ ባሳለፉ ሃገራት ሃራቸውን በከፍተኛ ዲፕሎማትነት ያገለገሉት ሳተርፊልድ ፌልትማንን እስከተኩበት ጊዜ ድረስ በቱርክ የአሜሪካ አምባሳደር ነበሩ።