ከሁለት አመት በፊት ኬንያ ጅቡቲን በሁለተኛ ዙር ምርጫ በማሸነፍ ነበር ለተመድ የጸጥታ ምክርቤት አባልነት የተመረጠችው
ሞዛምቢክ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) የፀጥታው ምክር ቤትን ለመጀመሪያ ጊዜ ተቀላቅላለች።
በአመቱ መጨረሻ የስልጣን ዘመኗን የምታጠናቅቀውን ኬንያን ለመተካት የአፍሪካ ሀገራት በሙሉ ድምፅ ተመርጣለች። ኢኳዶር፣ ጃፓን፣ ማልታ፣ ሞዛምቢክ እና ስዊዘርላንድ እንዲሁ ከፈረንጆቹ ጥር አንድ ጀምሮ ለሁለት ዓመታት የስልጣን ዘመን ተመርጠዋል።
አምስቱም ሀገራት የአለም አቀፍ ሰላምና ደህንነትን የማስጠበቅ ኃላፊት ባለው እና 15 አባላት ም/ቤት ያለምንም ተቃውሞ ተመርተዋል፡፡ህንድ፣ አየርላንድ፣ ኬንያ፣ ሜክሲኮ እና ኖርዌይን ይተካሉ።
ፕሬዝዳንት ፊሊፔ ኒዩሲ በፈረነጆቹ ከ2017 ጀምሮ ሞዛምቢክ በሁለት አመት የጸጥታው ም/ቤት የስልጣን ዘመኗ ሽብርተኝነትን ዋና ትኩረት ታደርጋለች ብለዋል፡፡ ሞዛምቢክ ለአየር ንብረት ለውጥ ፣ መደበኛ ጎርፍ እና ድርቅ የምትጠቃቀ በደቡባዊ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ነች፡፡
ከሁለት አመት በፊት ኬንያ ጅቡቲን በሁለተኛ ዙር ምርጫ 129 የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ድምጽ በማሸነፍ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን (ተመድ) የጸጥታ ምክርቤት ቋሚ ያልሆነ መቀመጫ ማሸነፍ ይታወሳል፡፡
ኬንያ ከአፍሪካ ህብረት ጋር ጠንካራ ግንኙነት አላት ያሉት የኬንያው ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የኬንያ የዲሞክራሲና ከብዙ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት አውስተው ነበር፡፡ፕሬዘዳንቱ ኬንያ የምታሸንፍ ከሆነ የአፍሪካን አጀንዳ ወደ ፊት እንዲመጣና አለምአቀፍ ወንድማማችነት እንዲጎለብት እንደምትሰራም በወቅቱ ገልጸው ነበር፡፡
ከኬንያ ጋር ሜክሲኮ፣ ህንድ፤አየርላንድና ኖርዌይ ለተመድ የጸጥታው ም/ቤት አባልነት ተመርጠው ነበር፡፡