ቢሊየነሩ ኢለን መስክ በአሜሪካ ስራ የጀመረው በህገወጥ መንገድ ነው ለሚለው ሪፖርት ምን ምላሽ ሰጠ?
ዋሽንግተን ፖስት በደቡብ አፍሪካ የተወለደው ቢሊየነር ኢለን መስክ በ1990ዎቹ ለአጭር ጊዜ አሜሪካ ውስጥ በህገወጥነት ሰርቷል ሲል ዘግቦ ነበር
መስክ ግን በእዚያ ወቅት አሜሪካ ውስጥ እንዲሰራ ተፈቅዶልኝ ነበር ሲል የዋሽንግተን ፖስትን ሪፖርት አስተባብሏል
ቢሊየነሩ ኢለን መስክ በአሜሪካ ስራ የጀመረው በህገወጥ መንገድ ነው ለሚለው ሪፖርት ምን ምላሽ ሰጠ?
ዋሽንግተን ፖስት በደቡብ አፍሪካ የተወለደው የአለም ቁጥር አንዱ ቢሊየነር ኢለን መስክ በ1990ዎቹ ለአጭር ጊዜ አሜሪካ ውስጥ በህገወጥነት ሰርቷል የሚል ሪፖርት አውጥቶ ነበር።
መስክ ግን በእዚያ ወቅት አሜሪካ ውስጥ እንድሰራ ተፈቅዶልኝ ነበር ሲል የዋሽንግተን ፖስትን ሪፖርት አስተባብሏል።
መስክ አክሎም "ኤች1-ቢ ቪዛ ከማግኘቴ በፊት ጄ-1 ቪዛ ነበረኝ" ሲል በኤክስ ገጹ ጽፏል። ጄ-1 ቪዛ የውጭ ሀገር ተማሪዎች አሜሪካ ውስጥ የትምህርት ስልጠና እንዲያገኙ የሚፈቅድ ሲሆን ኤች1-ቢ ቪዛ ደግሞ በጊዜያዊነት እንዲቀጠሩ የሚያስችል ነው።
ጋዜጣው መስክ በ1995 በፕሎ አልቶ ካሊፎርንያ በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ለመማር መምጣቱን፣ ነገርግን የድህረ ምረቃ ትምህርቱን እንዳልጀመረ ዘግቧል።
ዘገባው አክሎም መስክ 'ዚፕ 2' የተባለ የሶፍትዌር ኩባንያ መመስረቱን እና በ1999 መሸጡን ጠቅሷል። ጋዜጣው ሁለት የኢምግሬሽን ህግ ባለሙያዎችን ጠቅሶ መስክ በሰአቱ የስራ ፈቃዱ ህጋዊ እንዲሆን ትምህርቱን ማጠናቀቅ ይጠበቅበት ነበር ሲል ዘግቧል።
እንደባለሙያዎቹ ከሆነ አለምአቀፍ ተማሪዎች ምንም እንኳን ክፍያ ወይም ደሞዝ ባይከፈላቸውም ከዩኒቨርሲቲ ወጥተው ስራ እንዲጀምሩ አይፈቀድላቸውም ነበር። ባለሙያዎቹ ከመስከረም 11፣2011 ወዲህ የተማሪዎችን ቪዛ የሚመለከቱ ህጎች እንደቀለሉ ተናግረዋል።
ቪዛቸው ካለቀ በኋላ የሚቆዩ ተማሪዎች አልፎ አልፎ የነበሩ እና አንዳንድ ባለስልጣናት የሚያልፏቸው ቢሆንም ህገወጥ ነበሩ።
የዋሽንግተን ፖስት አዲሱ መረጃ ደቡብ አፍሪካዊው ቢሊየነር መስክ ከያዘው ጸረ-ስደተኛ አቋም ጋር የሚቃረን እንደሆነ ይጠቅሳል።
መስክ ምክትል ፕሬዝደንት የሆኑት ካማላ ሃሪሰን እና ዲሞክራቲክ ፖርቲን በህገ ወጥ ስደት አማካኝነት "መራጮችን በማስገባት" ከሷል። እንደሪፖርቱ ከሆነ መስክ ለትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ 119 ሚሊዮን ዶላር ለግሷል።
ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ደግሞ ይህን ሪፖርት ከትራምፕ ጋር የሚወዳደሩትን ሀሪስን ለመደገፍ ተጠቅመውበታል።
በፒትስበርግ በተካሄደው ሁነት ላይ ፕሬዝደንት ባይደን "ትምህርት ቤት መሆን የሚገባው የአለም ሀብታሙ ሰው አሜሪካ ውስጥ ህገወጥ ነበር።"