ማርክ ዙከርበርግ “ከኤለን መስክ ጋር የቡጢ ፍልሚያ ጉዳይን ብንተወው ሳይሻል አይቀርም” አለ
የፌስቡክ መስራቹ ማርክ ዙከርበርግ “ከኤለን መስክ ቦክስ እንጋጠም ያለው የምሩን አይደለም” ብሏል
ኤለን መስክ በሰጠው ምለሽ የፌስቡክ መስራቹ ማርክ ዙከርበርግን “ፈሪ” ብሎታል
የፌስቡክ መስራቹ እና የሜታ ክባንያ ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ “ከኤለን መስክ ጋር የቡጢ ፍልሚያ ጉዳይን ብንተወው ሳይሻል አይቀርም” አለ።
የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ ኢለን መስክ ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ ነበር ለተፎካካሪው የሜታ ኩባንያ ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ የእንፋለም ጥያቄ ያቀረበው፡፡
ዙከርበርግም የኢለን መስክ ጥያቄ መቀበሉን ከተናገረ በኋላ ሁለቱም አካላት በየግላቸው ልምምድ በመስራት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የሁለቱ አሜሪካዊያን ፍልሚያ የብዙዎችን ትኩረት የሳበ ሲሆን ፍልሚያው የሚካሄድበት ቦታም ባሳለፍነው አርብ ይፋ የተደረገ ሲሆን፤ ውድድሩ በጣልያን መዲና ሮም እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ይሁን እንጂ የፌስቡክ መስራቹ እና የሜታ ክባንያ ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ ትሪድስ በተባለ አዲሱ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሁፍ፤ ኤለን መስክ ስለ ቦክስ ፍልሚያው የምሩን አይደለም፤ ሰለዚህ ብንተወው ሳይሻ አይቀርም ብሏል።
ማርክ ዙከርበርግ ባለፈው ሳምንት ከኤለን መስክ ጋር የቦክስ ፍልሚያው በፈረንጆቹ ነሐሴ 26 ይከናውን ሲል ቀን ቆርጦ ነበር።
ዛከርበርግ “ኤላን ቀን ሊቆርጥ አልቻለም፤ አንዴ ቀዶ ጥገና ያስፈልገኛል ይላል፤ አንድ ጊዜ ደግሞ እኔ ቤት ጓሮ የሙከራ ድብድብ እናድርግ ይላል” ሲል አስታውቋል።
ኤለን መስክ ስለ ቦክስ ፍልሚያው የምሩን ከሆነ እንኔን እንዴት ማግኘት እንደሚችል ያውቃል፤ ስለዚህ አግኝቶኝ ያሳውቀኝ፤ ካለሆነ ግን ብንተወው ይላል ብሏል።
ኤለን መስክ በአዲሱ ስሙ ኤክስ በተባለው የቀድሞ ትዊተር ማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ በሰጠው ምለሽ የፌስቡክ መስራቹ እና የሜታ ክባንያ ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ “ፈሪ” ብሎታል።
ኤለን መስክ እና ማርክ ዙከርበርግ በቴክኖሎጂ ፉክክር ውስጥ ያሉ ስራ ፈጣሪዎች ሲሆኑ ሜታ ኩባንያ ከሁለት ወር በፊት ይፋ ባደረገው ትሪድስ የተሰኘው የማህበራዊ ትስስር ገጽ ክስ ቀርቦበታል።
ኢለን መስክ በሜታ ለይ ክስ የመሰረተው በቀድሞ ስሙ ትዊተር ኩባንያ ከስራ የተሰናበቱ ሰራተኞችን በመቅጠር የድርጅቴን ሚስጢሮች ወስዶብኛል በሚል ነው።