ናይጀሪያዊው የማርሻል አርት ባለሙያ ኢስራኤል አዴሲና ማርክ ዙከርበርግን ማሰልጠን ጀመረ
ዝነኞቹ ባለጸጋ ኢለን መስክ እና ማርክ ዙከርበርግ በቡጡ ሊፋለሙ ቀጠሮ መያዛቸው ይታወሳል
ኢለን መስክ በበኩሉ በታዋቂው አሜሪካዊ የቡጢ ተፋላሚ ጆርጅ ፒሬ በመሰልጠን ላይ ነው
ናይጀሪያዊው የማርሻል አርት ባለሙያ ኢስራኤል አዴሲና ማርክ ዙከርበርግን ማሰልጠን ጀመረ።
ሁለቱ እውቅ ስራ ፈጣሪ አሜሪካዊያን ኢለን መስክ እና ማርክ ዙከርበርግ የዓለማችን ባለጸጋዎች ናቸው።
ለአያሌ የአለም ዜጎች የስራ እድል የፈጠሩት እነዚህ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ባለቤቶች ከአንድ ወር በፊት ነበር እንደቀልድ በቡጢ ለመናረት የተስማሙት።
የቴስላ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባለቤት፣ የትዊተር እና ሌሎች ኩባንያዎችን የመሰረቱት ኢለን መስክ በሀብት መጠናቸው የዓለማችን ቀዳሚው ሰው ናቸው።
ኢለን መስክ ከወራት በፊት በገዙት ትዊተር ገጻቸው ላይ የፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ትሪድስ የተሰኙ የማህበራዊ ትስስር ኩባንያ ባለቤት ለሆኑት ማርክ ዙከርበርግ ለምን አንቧቀስም? ሲሉ ጥሪ አቀረቡ።
ማርክ ዙከርበርግም ብዙም ሳይቆዩ ከኢለን መስክ የቀረበላቸውን የእንጋጠም ጥያቄ መቀበላቸውን ከገለጹ በኋላ ጉዳዩ የዓለም ዋነኛ መነጋገሪያ ጉዳይ ሆኗል።
የሁለቱ ባለጸጋዎች የውድድር ቦታ እና ጊዜ እስካሁን ይፋ ያልሆነ ሲሆን እስከዛው ግን ሁለቱም ሰዎች ልምምድ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ማርክ ዙከርበርግ በትውልደ ናይጀሪያዊው የማርሻል አርት ተፋላሚ እስራኤል አዴሲና እየሰለጠነ ሲሆን ኢለን መስክ ደግሞ በሌላኛው የአለማችን የማርሻል አርት ተፋላሚ ጆርጅ ፒሬ ስልጠና ላይ ነው ተብሏል።
የሁለቱ ባለጸጋዎች የእንፋለም ወሬ ሲሰማ ብዙዎች የምር ላይፋለሙ ይችላሉ ቢሉም ሰዎቹ የምር ልምምድ መጀመራቸው ሲሰማ እውነት ሊፋለሙ ይሆን እንዴ እየተባለም ይገኛል።
በተቃራኒው ደግሞ ሁለቱ ባለጸጋዎች ፍልሚያውን አስቀድመው ጀምረውታል የተባለ ሲሆን በተለይም የትዊተር እና ትሪድስ ጉዳይ ዋነኛ የፍልሚያ ጉዳይ ሆኗል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
የሁለቱ ተቀናቃኝ ኩባንያ ባለቤቶች አለመግባባት ወደ ፍርድ ቤት ያሙራ ሲሆን ትሪድስ የተመሰረተው ከትዊተር በተቀነሱ ሰራተኞች ነው ፣ ሜታ ኩባንያ ሚስጥሬን ወስዷል የሚል ክስ ከትዊተር ቀርቦበታል።