ቢሊየነሩ መስክ ዩኤስኤአይዲን "እንዳያንሰራራ" አድርጎ ለመዝጋት እየሰራ እንደሚገኝ አስታወቀ
ትራምፕ መስክን የፌደራል መንግስታት ወጭ ቅነሳ ስራ እንዲመራ ሾመውታል
"ቅድሚያ ለአሜሪካ" የሚል ፖሊሲ የሚያራምዱት ትራምፕ አብዛኛው የአሜሪካ እርዳታ እንዲቆም ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው አለምን አስደንግጧል
ቢሊየነሩ መስክ ዩኤስኤአይዲን "እንዳይድን" አድርጎ ለመዝጋት እየሰራ እንደሚገኝ አስታወቀ።
የፕሬዝደንት ትራምፕን የፌደራል መንግስት ወጭ የመቀነስ ጥረት እየመራ ያለው ቢሊየነሩ ኢሎን መስክ የአሜሪካ የውጭ እርዳታ ድርጅትን(ዩኤኤአይዲን) ለመዝጋት እየሰራ እንደሚገኝ በዛሬው እለት አስታውቋል።
የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ቴስላና የስፔስኤክስ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆነው መስክ የመንግስት ቀልጣፋ አሰሳር መስሪያ ቤትን(ዶጅ) በተመለከተ በኤክስ ገጹ ወይይተ አድርጓል።
ትራምፕ መስክን የፌደራል መንግስታት ወጭ ቅነሳ ስራ እንዲመራ ሾመውታል።
በውይይቱ የቀድሞ የሪፐብሊካን ፕሬዝደንታዊ እጩ ቪቬክ ራምስዋሚና የሪፐብሂካን ሴናተሮች ጆኒ ኢርነስትና ማይክ ሊን ያካተተ ሲሆን መስክ ዩኤስአይዲን ለመዝጋት እየሰሩ እንደሆነ በመግለጽ ወይይቱን ከፍቷል።
"መትረፍ የለበትም" ያለው መስክ ጨምሮም ፕሬዝደንት ትራምፕ መዘጋት አለበት በሚለው መስማማታቸውን ገልጿል።የዩኤስአይዲ ሁለት ከፍተኛ የደህንነት ባለስልጣናት መስክ ከሚመራው የመንግስት ቀልጣፋ አሰራር ቢሮ ለተላኩ ተወካዮች ጥብቅ ቁጥጥር ወደሚደረግበት የህንጻ ክፍል እንዳይገቡ መከልከላቸውን ተከትሎ በትራምፕ አስተዳደር መባረራቸውን ሮይተርስ ምንጮችን ጠብሶ በትናንትናው እለት ዘግቦ ነበር።
የዩኤስኤአይዲ በአለም ብቸኛ ከሆኑት የእርዳታ ተቋማት ከፍተኛ እርዳታ የሚያቀርብ ነው።
በ2ዐ23 የበጀት አመት በግጭት ውስጥ ለሚገኙ ሴቶች፣ ለንጹህ መጠጥ ውሃ፣ ለኤችአይቪና ኤድስ፣ ለኃይል ዋስትና ለጸረ-ሙስና ስራ የሚውል የ72 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ አድርጓል።
ድርጁቱ 42 በመቶ ድጋፉን የሚሰጠው በተመድ ቁጥጥር በሚደረግበት የሰብአዊ እርዳታ ላይ ነው።
የዩኤስአይዲ ድረ-ገጽ ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ተደራሽነቱ የተቋረጠ ሲሆን የተወሰኑ ተጠቃሚዎች በትናንትናው እለት መግባት እንዳልቻሉ ሮይተርስ ዘግቧል። ድርጁቱ ከ10ሺ በላይ ሰራተኞች አሉት።
"ቅድሚያ ለአሜሪካ" የሚል ፖሊሲ የሚያራምዱት ትራምፕ አብዛኛው የአሜሪካ እርዳታ እንዲቆም ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው አለምን አስደንግጧል።
መስክ ስለአሜሪካ ወጭና ማጭበርበር ቅነሳና ሲናገር የትራምፕ አስተዳደር እስከ አንድ ትሪሊየን ዶላር ወጭ መቀነስ ይችላል ሲል ግምቱን አስቀምጦ ነበር።
መስክ "ልምድ ያላቸው የውጭ አጭበርባሪዎች" ዲጂታል የአሜሪካ ዜጋ በመምሰል ብዙ ገንዘብ እንደሚያጭበረብሩ ገልጸዋል። ነገርግን መስክ ይህን ሀሳባቸውን የሚደግፍ ወይም እንዴት አንድ ትሪሊዮን እንደሚደርስ መረጃ አላቀረበም።
መስክ በትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ደጋፊ ከነበሩ ባሀብቶች ውስጥ ቀዳሚው ነው።