የሚያንማር ጦር አባል የሆኑት ስድት ወታደሮች አቅመ ደካሞችን መግደላቸው እንደሚጸጽታቸው ገልጸዋል
የሚያንማር ወታደሮች በሰው ልጆች ላይ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት መፈጸማቸውን ማመናቸው ተሰምቷል።
ቢቢሲ ቃለ መጠይቅ እንዳደረገላቸው የገለጻቸው የሚያማር ጦር አባል የሆኑት ስድት ወታደሮች የሰው ልጆችን መግደላቸውንና ማሰቃየታቸውን ገልጸዋል ብሏል።
ወታደሮቹ ሴቶችን መድፈራቸውንም እንዳመኑ ነው የቢቢሲ ዘገባ የሚያመለክተው።
ወታደሮቹ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውን የገለጹት ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑንም ሚዲው ዘግቧል። የሚያንማር ወታደራዊ አዛዦች የመብት ጥሰቶች እንዲፈጸሙ ትዕዛዝ ስለመስጠታቸውም ነው ወታደሮቹ ያነሱት።
ወታደሮቹ ይህንን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲፈጽሙ ቀጥታ ትዕዛዝ ይመጣላቸው እንደነበርም ምስክርነት ሰጥተዋል።
አዛዦቹ የመብት ጥሰት እንዲፈጸም፤ ዝርፊያ እንዲካሄድና ንጹሃን እንዲገደሉ ትዕዛዝ ይሰጡ ነበርም ተብሏል።
የሚያምናር ወታደሮች በገዳም የተደበቁ ንጹሃንን መግደላቸውም ነው የተሰማው። ወታደሮቹ አቅመ ደካሞችን መግደላቸው አሁን ላይ እንደሚጸጽታቸው መግለጻቸውም ተገልጿል።
ከስልጣናቸው በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት የተነሱት የሚይንማር መሪ ኦንግ ሳን ሱ ኪ የ4 ዓመት እስር እንደተፈረደባቸው ተገልጿል።