ናሚቢያ እገዳውን የጣለቸው በሁለቱ ሀገራት የወፍ ጉንፋን መከሰቱን ተከትሎ ነው
ናሚቢያ የዶሮ ስጋ እና እንቁላል ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ አገደች፡፡
ደቡብ አፍሪካዊቷ አገር ናሚቢያ ዶሮ እና እንቁላል ከጀርመን እና ኔዘርላንድ ወደ አገሯ እንዳይገቡ እገዳ ጥላለች፡፡
ሀገሪቱ ወደዚህ ውሳኔ የመጣችው በሁለቱ አገራት የወፍ ጉንፋን መከሰቱን ተከትሎ እንደሆነ ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል፡፡በጀርመን እና ሆላንድ የወፍ ጉንፋን መከሰቱን ያሳወቁ ሲሆን የዶሮ አርቢዎች ምርቶቻቸውን ወደ ገበያ እንዳያወጡ አገራቱ አስጠንቅቀዋል፡፡
ይሄንን ተከትሎም የናሚቢያ እንስሳት ጤና አገልግሎት ከጀርመን እና ኔዘርላንድ ወደ አገሯ የሚመጡ ወይም በአገሯ ኣድርጎ ወደ ሌሎች አገራት የሚደረጉ ጉዞዎችን መታገዱን አስታወቋል፡፡
ከአንድ ወር በፊት ከጀርመን ው ዊንድሆክ ለማምጣት በሚል የተገዙ የዶሮ ስጋ ምርቶች በጉዞ ላይ ቢሆኑም ወደ ሀገራቸው ከመግባቱ በፊት እንዲመለስ ወይም እንዲቃጠሉ ሊደረግ እንደሚችልም ተቋሙ አስታውቋል፡፡