ዩ.ኤ.ኢ ከላይቤሪያ፣ ሴራሊዮንና ናሚቢያ የሚነሱ መንገደኞችን ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ አገደች
እገዳው የተጣለው በሀገራቱ ባለው ከፍተኛ ኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት እንደሆነም ተገልጸዋል
እገዳው ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋልም ነው የተባለው
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከሰኞ ቀን ጀምሮ ከላይቤሪያ ፣ ሴራሊዮን እና ናሚቢያ የሚነሱ መንገደኞች ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ እገዳ መጣሏን የሀገሪቱ ሲቪል አቪዬሽን ዋና ባለስልጣን አስታውቀዋል፡፡
ሀገሪቱ እገዳውን የጣለችው በሀገራቱ ያለው ወቅታዊ የኮረና ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ነው፡፡
እገዳው ባለፊት ሁለት ሳምንታት በሀገራቱ የቆይቱንና ያልመጡትን መንገደኞች እንደሚያከትትም ነው የኤምሬትስ ዜና ኤጀንሲ የዘገበው።
ይሁን እንጂ እገዳ ከተጣለባቸው ሀገረት ውጭ የሚመጡት ሰዎች በተለይም ደግሞ የኤሜሬቶች ዜጎች፣ የንጉሳውያን ቤተሰቦች፣ ዲፕላማቲክ እና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት እንዲሁም በሀገራቱ በሚገኙ የኤምሬት ኤምባሲዎች የሚሰሩ አስተዳደሮች እና ተወካዮች አስፈላጊውን የኮቪድ ምርመራ አሰራርን በተከተለ መልኩ ይስተናገሰዳሉ ተብለዋል።
የአቬሽን ባለስልጣኑ በሌላ ሀገራት በኩል የሚመጡ የሶስቱም ሀገራት መንገደኞች ወደ ኤሜሬቶች ለመግባት ለ14 ቀናት ያክል በለይቶ ማቆያ ውስጥ ይቆያሉም ብለዋል።
ባለስልጣኑ እገዳው ከመጣሉ ጋር በተያያዘ ለተስተጓጎሉ መንገደኞች በቀጣይ የሚኖረውን ማስተካከያና የበረራ መርሃ-ግብር ለማወቅ እንዲችሉ የአየር መንገዱን ወቅታዊ መረጃዎች እንዲከታተሉ አሳስበዋል።
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ከዚህ ቀደምም ከዛምቢያ፣ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ከኡጋንዳ የሚነሱ መንገደኞች ወደ ሀገሯ መግባት እንደማይችሉ ማስታወቋ ይታወሳል።