ምናጋግዋን ፕሬዘዳንት ሆነው የተመረጡት ፕሬዝዳንት ሮበርቶ ሙጋቤን በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን ከተነሱ በኋላ ነበር
የዚምባብዌ ገዥው ፓርቲ ፕሬዘዳንት ምናጋግዋን በቀጣዩ ምርጫ እጩ አድርጎ ማቅረቡን አስታውቋል፡፡
ደቡብ አፍሪካዊቷ ሀገር ዚምባብዌ በፈረንጆቹ 2023 ዓመት ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ እንደምታካሂድ የሀገሪቱ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡
የዚምባብዌ ገዢው ፓርቲ ዛኑ-ፒኤፍ የወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት ኤመርሰን ምናጋግዋ በቀጣዩ ምርጫ እጩ መሆናቸውን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል፡፡
ፓርቲው ይሄንን ያሳወቀው ባካሄደው ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ሲሆን ከፈረንጆቹ 2018 ዓመት ጀምሮ ሀገሪቱን በመምራት ላይ ያሉት ምናጋግዋ እጩ መሆናቸውን ገልጿል፡፡
ፕሬዘዳንት ምናጋግዋ ከሶስት ዓመት በፊት ዚምባብዌን ለ37 ዓመታት የመሩት ሮበርት ሙጋቤ በህዝብ ተቃውሞ እና በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን መነሳታቸውን ተከተሎ ነበር ወደ ስልጣን የመጡት፡፡
15 ሚሊዮን ገደማ የህዝብ ብዛት እንዳላት የሚነገርላት ዚምባብዌ ወደብ አልባ አገር ስትሆን ደቡብ አፍሪካ፤ዛምቢያ ፤ ሞዛምቢክ እና ቦትስዋና ያዋስኗታል፡፡
ምናጋግዋን ፕሬዘዳንት ሆነው የተመረጡት ዚባብዌን ለረጅም አመታት የመሩትን ፕሬዝዳንት ሮበርቶ ሙጋቤን በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን ከተነሱ በኋላ ነበር፡፡