በ7 ሰዓታት ውስጥ የበረሃ አሸዋን ወደ ለም አፈርነት የሚለውጠው ቴክኖሎጂ
የኖርዌይ ኩባያ በረሃማነትን በብቃት መዋጋት የሚየስችል አዲስ ፈጠራ ማግኘቱን አስታውቋል
አዲሱ ፈጠራ በበረሃማ አካባቢዎች በቀላሉ የግብርና ምርቶችን ለማምረት ያስችላል ተብሏል
የኖርዌይ ኩባንያ በረሃማትን ለመከላከለ የሚያስች አዲስ የፈጠራ ስራ ይዞ ብቅ ማለቱን ከሰሞኑ አስታውቋል።
አዲሱ ፈጠራ በሰባት ሰዓታት ውስጥ የበረሃ አሸዋን ወደ ለም አፈርነት የሚለውጥ መሆኑንም ኦዲቲ ሴንትራል ይዞት በወጣው መረጃው አመላክቷል።
ይህ ፈጠራ “ናኖክሌይ” የተባለ ፈሳሽ ሲሆን፤ ፈሳሹ በበረሃ አሸዋ ላይ ከተረጨ ከሰዓታት በኋላ ወደ ለም አፈርነት የሚለውጥ መሆኑ ተነግሯል።
በኖርዌየዊው ተመራማሪ ክርስቲያን ኦልሰን ለመጀመሪያ ጊዜ በ2000 መጀመሪያ አካባቢ የተገኘው ይህ ፈጠራ በረሃማነትን በመቆጣጠር ረገት አመርቂ ውጤት የሚያመጣ እንደሆነ ተነግሮለታል።
ይህ አስደናቂ ፈጠራ በአሸዋ ላይ በሚረጭበት ጊዜ ወደ ታች ወርዶ አሸዋውን የሚያክም ሲሆን፣ ይህም እፅዋት የሚበቅሉበት ውሃ ወደ ሚይዝ አፈር ይለውጠዋል።
አርሶ አደሮች የመሬታቸውን ምርታማነት ለማሳደግ የሸክላ አፈርን ለብዙህ ሺህ ዓመታ ሲጠቀሙበት እንደነበረ የሚታወቅ ሲሆን፤ ናይል ዴልታ አካባቢ በዚህ የሸክላ አፈርን በመጠቀም ምርት እንደሚያመርቱም በብዛት ይታወቃል።
አዲሱ ፈጠራም ይህንን የሸክላ አፈር በመጠቀም ወደ ፈሳሽነት እና ጥቃትን ውህድንተ በመቀየር የተሰራ ሲሆን፤ በዚህም ናኖክሌይ የተባለው ፈጠራ መሰራቱ ተመላክቷል።
አዲሱ ናኖክሌይ ፈጠራ ውሃ እና የሸክላ አፈርን በመጠቀም የተሰራ ሲሆን፤ ሸክላው በውሃ መጠን እንዲቀጥን እና እንዲረጭ በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ ነው ተብሏል።
በዚህ መልኩም አንድ ስኩዌር ሜትር የበረሃ አሸዋማ ስፍራን ለማከም 2 እስከ 5 የአሜሪካ ዶላር ድረስ እንደሚፈጅ ሲ.ኤን.ኤን ከዚህ ቀደም ባወጣው ዘገባው አመላክቷል።