ፖለቲካ
ናኢም ቃሲም - የሄዝቦላህ አዲሱ መሪ
የሄዝቦላህ መስራችና ለረጅም አመታት የቡድኑ ምክትል መሪ ሆነው ያገለገሉት ሼክ ናኢም ቃሲም በእስራኤል የተገደሉትን ሀሰን ናስራላህ እንዲተኩ ተመርጠዋል
እስራኤል አዲሱ የሄዝቦላህ መሪ የናስራላህ እና ሃሽም ሰይፈዲን እጣ ሊገጥማቸው እንደሚችል ዝታለች
የሊባኖሱ ሄዝቦላህ በመስከረም ወር በእስራኤል ጥቃት የተገደሉትን ሀሰን ናስራላህ ተተኪን መርጧል።
ናስራላህን ይተካሉ ተብለው ሲጠበቁ የነበሩት ሃሽም ሰይፈዲን በእስራኤል ጥቃት መገደላቸውን ተከትሎ ሼክ ናኢም ቃሲም የቡድኑ መሪ እንዲሆኑ የሄዝቦላህ ሹራ ምክርቤት መወሰኑ ተገልጿል።
ሄዝቦላህን ከመመስረት ጀምሮ ከ30 አመታት በላይ በተለያዩ የሃላፊነት ስፍራዎች ያገለገሉት ቃሲም የፖለቲካ ተሳትፏቸውን አሃዱ ያሉት በፈረንጆቹ 1974 በተመሰረተው የሊባኖስ ሺያ አማል ንቅናቄ ውስጥ ነው።
በ1991 የወቅቱ የሄዝቦላህ መሪ አባስ አል ሙሳዊ ምክትላቸው እንዲሆኑ የመረጧቸው ሼክ ናኢም ቃሲም፥ አል ሙሳዊ በ1992 በእስራኤል ከተገደሉ በኋላ ሀሰን ናስራላህ መሪነቱን ሲረከቡም በሃላፊነታቸው ዘልቀዋል።
የእስራኤል መንግስት ባወጣው መግለጫ አዲሱ የሄዝቦላህ መሪ የናስራላህ እና ሃሽም ሰይፈዲን እጣ ሊገጥማቸው እንደሚችል ዝቷል።
የሄዝቦላህ ወታደራዊ አቅም ሙሉ በሙሉ እስኪፈራርስ ድረስ ጦርነቱ እንደሚቀጥልም ነው ያስታወቀው።
አዲሱ የሄዝቦላህ መሪ ማን ናቸው የሚለውን በቀጣዩ ምስል ይመልከቱ፦