የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽነር የነበሩት አምባሳደር ተሾመ ከኃላፊነት ለቀቁ
የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን የተቋቋመው በሰሜን ኢትዮጵያ በፌደራል መንግስት እና የትግራይ ክልልን ሲያስተዳደር በነበረው ህወሓት መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት በፕሪቶሪያው የዘላቂ ሰላም ስምምነት ማብቃቱን ተከትሎ ነበር።
የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በገዛ ፍቃዳቸው ከኃላፊነት መልቀቃቸውን ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል
የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽነር የነበሩት አምባሳደር ተሾመ ከኃላፊነት ለቀቁ።
የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በገዛ ፍቃዳቸው ከኃላፊነት መልቀቃቸውን ኮሚሽኑ በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ኮሚሸኑ በመግለጫው አምባሳደር ተሾመ በግል ጉዳያቸው ምክንያት ለመልቀቅ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን እና በዚህ መሰረት ከመጋቢት 3/2016 ጀምሮ ከኃላፊት መልቀቃቸውን ጠቅሷል።
ከኃላፊነት በለቀቁት አምባሳደር ተሾመ ምትክ አቶ ተመስገን ጥላሁን የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሸን ኮሚሽነር ሆነው ተሾመዋል ብሏል መግለጫው።
ኮሚሽኑ እንደገለጸው የኮሚሾኑ የሎጂስቲክ እና የአስተዳደር ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር የነበሩት ዶክተር አትንኩትም ከኃላፊነት ተነስተው በተስፋአለም ይህደጎ ተተክተዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ኮሚሽኑን በበላይነት ለመምራት በፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ የሚመሩ አምስት የቦርድ አመራሮች ተሰይመዋል።
የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን የተቋቋመው በሰሜን ኢትዮጵያ በፌደራል መንግስት እና የትግራይ ክልልን ሲያስተዳደር በነበረው ህወሓት መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት በፕሪቶሪያው የዘላቂ ሰላም ስምምነት ማብቃቱን ተከትሎ ነበር።
ኮሚሽኑ በጦርነት ተሳታፊ የሆኑ መደበኛ ያልሆኑ ታጣቂዎች ትጥቃተቸውን ፈትተው ወደ ሰላማዊ ህይወታቸው እንዲመለሱ የማድረግ አላማ እንዳለው መግለጹ ይታወሳል።