ኔቶ ከቀዝቃዛው ጦርነት በኋላ የመጀመሪያውን የመከላከያ እቅድን ለማጽደቅ ተሰብስቦ ሳይስማማ ተለያየ
ወታደራዊ እቅዶችቹ ህብረቱ ለሩስያ ጥቃት እንዴት ምላሽ እንደሚሰጥ በዝርዝር ይገልጻል ተብሏል
የኔቶ አባል ሀገራት ላለመስማታቸው ቱርክን ተወቅሳለች
የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን (ኔቶ) መከላከያ ሚንስትሮች ህብረቱ ለሩሲያ ጥቃት ምላሽ ይሰጣል በተባለው አዲስ እቅድ ላይ ስምምነት ላይ መድረስ አልቻሉም።
ለዚህም የቱርክ አለመስማማት ምክንያት ነው ተብሏል።
የኔቶ ዋና ጸሃፊ የንስ ስቶልተንበርግ ሚንስትሮቹ እቅዶቹን ከቀዝቃዛው ጦርነት ማብቂያ በኋላ የመጀመሪያው እና ሩሲያ በዩክሬን ላይ ባደረገችው ወረራ መነሳሳትን ገምግመው ለመስማማት እየተቃረቡ ነበር ብለዋል።
ነገር ግን አንድ ዲፕሎማት ቱርክ መልከዓምድራዊ አቀማመጦችን በመጥቀስ ፈቃድ ከልክላለች ብለዋል። በሀምሌ ወር አጋማሽ በቪልኒየስ በሚካሄደው የኔቶ ስብሰባ ሁለተኛ እድል እንዳለ ዲፕሎማቱ አክለዋል።
በኔቶ የቱርክ ዲፕሎማሲያዊ ልዑክ በኔቶ ሚስጥራዊ ሰነድ ላይ አስተያየት መስጠት ስህተት መሆኑን ገልጾ "በአጋሮች መካከል የተለመደው የምክክር እና የግምገማ ሂደት ቀጥሏል" ብሏል።
"የቀጠናዊ እቅዶች" የተባሉሉት በሺዎች የሚቆጠሩ ገጾች ሚስጥራዊ ወታደራዊ እቅዶችን ያያዘ ሲሆን ይህም ህብረቱ ለሩስያ ጥቃት እንዴት ምላሽ እንደሚሰጥ በዝርዝር ይገልጻል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
የሰነዶቹ ንድፍ መሰረታዊ ለውጥን ያመለክታልም ተብሏል።
ኔቶ ትናንሽ ጦርነቶችን በመዋጋቱ እና ከሶቪየት ህብረት በኋላ ሩሲያ የህልውና ስጋት አይደለችም በሚል ለበርካታ አስርት ዓመታት መጠነ-ሰፊ የመከላከያ እቅዶች አላደረገም።
ነገር ግን ከ1945 ወዲህ የአውሮፓ ደም አፋሳሽ በሆነው ጦርነት፣ እንደ ሞስኮ ካሉ ሀገራት ጋር ግጭት ከመፈጠሩ በፊት ህብረቱ እቅድ ማውጣት እንዳለበት እያስጠነቀቀ ነው።
ኔቶ አባል ሀገራት ኃይሎቻቸውን እና ትጥቃቸውን እንዴት ማሻሻል እንደሚችሉ መመሪያ ይሰጣል።