ኔቶ በሩሲያ ድንበር አቅራቢያ 90 ሺህ ወታደሮችን ያሳተፈ ልምምድ በማድረግ ላይ ይገኛል
የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን (ኔቶ) ከሩሲያ ጋር ለሚፈጠረው ግጭት በትኩረት እየተዘጋጀ መሆኑን ሞስኮ አስታወቀች።
ሩሲያ ከሰሞኑ እንዳስታወቀችው ከሆነ፤ ኔቶ ዘመናዊ እና ከባድ የጦር መሳሪያዎችን በመጠቀም በሀገሪቱ ድንበር አቅራቢያ ልምምድ ማድረግ ከጀመረ ሰነባብቷል።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛክሃሮቫ በሰጡት መግለጫ፤ ኔቶ በሩሲያ ድንበር አቅራቢያ እያደረገው ያለው ልምምድ ከቀዝቃዛው ጦርነት በኋላ ግዚፍ ወታደራዊ ልምምድ መሆኑን አስታውቀዋል።
“የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን (ኔቶ) ያሉትን ከባባድ የጦር መሳሪያዎች ሁሉ ተጠቅሞ በሩሲያ ላይ ሊወስድ የሚችለውን ጥቃት ሁሉ እያሳየ ነው” ብለዋል ቃል አቀባይዋ።
ቃል አቀባይዋ አክለውም "ኔቶ ከእኛ ጋር 'ሊፈጠር ለሚችል ግጭት' ትኩረት ሰጥቶ እየተዘጋጀ መሆኑን መቀበል አለብን" በማለት ተናግረዋል።
ኔቶ ግዙፍ የተባለውን ወታደራዊ ልምምድ ባሳለፍነው ጥር ወር የጀመረ ሲሆን፤ በልምምዱ ላይ 90 ሺህ የጥምረቱ አባል ሀገራት ወታደሮች መሳተፋቸው ተነግሯል።
ወታደራዊ ልምምዱ እስከ ግንቦት ወር ቀጥሎ ይካሄዳ የተባለ ሲሆን፤ ኔቶ ቀደም ሲል ወታደራዊ ልምምዱን “ከአቻ የቅርብ ጠላት የሚፈጠር የግጭት ቢሆኖች መከላከል” ሲል ገልጾታል።
31 አባል ሀገራትን ያቀፈው የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን (ኔቶ) ሩሲያን ከቅላልቅ ተቃማዊዎቹ ጎራ መፈረጁም የሚታወቅ ነው።