ሩሲያ ኔቶን አታጠቃም፤ ነገርግን ኤፍ-16 ጄቶችን እንደታንኮቹ ሁሉ መትታ ታወድማለች-ፑቲን
የሩሲያ በ2022 ዩክሬንን መውረር ከ1962 የኩባ ሚሳይል ቀውስ ወዲህ በሩሲያ እና ምዕራባውያን ግንኙነት ላይ ከባድ ችግር ፈጥሯል
ምዕራባውያን ለዩክሬን ኤፍ-16 የሚያስታጥቁ ከሆነ የሩሲያ ኃይሎች ጄቶቹን መትተው ይጥላሉ ሲሉ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ባለፈው ረብዕ ተናግረዋል
ሩሲያ የትኛውንም የኔቶ አባል ሀገር፣ ፖላንድን፣ የባልቲክ ሀገራትን ወይንም ቼክ ሪፐብሊክን የማጥቃት ፍለጎት የላትም፤ ነገርግን ምዕራባውያን ለዩክሬን ኤፍ-16 የሚያስታጥቁ ከሆነ የሩሲያ ኃይሎች ጄቶቹን መትተው ይጥላሉ ሲሉ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ባለፈው ረብዕ ተናግረዋል
የሩሲያ በ2022 ዩክሬንን መውረር ከ1962 የኩባ ሚሳይል ቀውስ ወዲህ በሩሲያ እና ምዕራባውያን ግንኙነት ላይ ከባድ ችግር ፈጥሯል።
ፑቲን ለሩሲያ አየር ኃይል ወታደሮች ከሶቬት ህብረት መውደቅ በኋላ በአሜሪካ የሚመራው ወታደራዊ ጥምረት ወደ ምስራቅ እየተስፋፋ ቢመጣም ሩሲያ የኔቶ ሀገራትን የማጥቃት እቅድ የላትም ብለዋል።
"እነዚህ ሀገራት ላይ ወረራ የመፈጸም አላማ የለንም" ብለዋል ፑቲን።
ፑቲን አክለው እንዳሉት "ሌሎች ሀገራትን እናጠቃለን ይባላል። ፖላንድ፣ የባልቲክ ሀገራት እና ቼክ ይሰጋሉ፤ ይህ ፍጹም ትርጉምየለሽ ነው።"
አሜሪካ ዩክሬንን በገንዘብ፣በጦር መሳሪያ እና በስለላ በመደገፍ ሩሲያን እየወጋች ነው ሲል የሚከሰው ክሬሚሊን ከዋሽንግተን ጋር የሚኖረው ግንኙት ከዚህ የባሰ ሊከፋ ይችላል ብሏል።
ምዕራባውያን ለዩክሬን ቃል ስለገቡት ኤፍ-16 የጦር ጄት የተጠየቁት ፑቲን እንዲህ አይነት ጀቶች በዩክሬን ያለውን ሁኔታ መቀየር እንደማይችሉ ተናግረዋል።
"ኤፍ-16 የጦር ጀቶችን ለዩክሬን ካቀረቡ እና በግልጽ አብራሪዎችን ካሰለጠኑ፣ በጦርሜዳ ያለውን ሁኔታ አይቀይረውም" ብለዋል ፑቲን።
ፑቲን ብዙ ሮኬት ማስወንጨፊያዎችንን እና ብረት ለበስ ታንኮችን እንዳወደምነው ሁሉ እነዚህን ጀቶችም መትተን እንጥላቸዋለን ብለዋል።
ፑቲን ኤፍ-16 ጀቶች ኑክሌር መሸከም የሚችሉ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
ፑቲን ይህን አስያየት የሰጡት የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሜትሮ ኩሌባ ኤፍ-16 ጀቶች በቅርቡ ዩክሬን ማለታቸውን ተከትሎ ነው።
ቤልጄየም፣ ዴንማርክ፣ ኖርዌይ እና ኔዘርላንድስ ኤፍ-16 ለመስጠት ቃል ከገቡ ሀገራት ውስጥ ይገኙበታል።
የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ሁለት አመት አልፎታል፤ ጦርነቱን በሰላም ለመቋጨት የተደረጉ ሙከራዎች አልተሳኩም።