የድርጅቱ የምስራቅ አውሮፓ መስፋፋት መቀጠልም የሩሲያን ስጋት ከፍ አድርጎታል
የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት ኔቶ በፈረንጆቹ 1949 ነው የተቋቋመው።
በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሌሎች 12 ሀገራት የተመሰረተው ድርጅት ሶቪየት ህብረትን ስጋት አድርጎ የተቋቋመ ወታደራዊ ጥምረት ነው።
ዋሽንግተን መራሹ ኔቶ አባል ሀገራቱንም ሆነ ወታደራዊ አቅሙንን እያፈረጠመ የምዕራባውያን ሀገራት የጋራ ደጀን መሆን መቻሉ ይነገራል።
አሜሪካ በአፍጋኒስታን የ20 አመታት ያልተሳካ ዘመቻ ስትደርግም የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ድርጅት አጋር ሆኖ መሰለፉ የሚታወስ ነው።
ሩሲያ በበኩሏ የኔቶ የምስራቅ አውሮፓ መስፋፋትን ስትቃወም የቆየች ሲሆን፥ ከዩክሬን ጋር ለገባችበት ጦርነትም ኬቭን የኔቶ አባል የማድረግ የምዕራባውያኑ ጥረት በምክንያትነት ታነሳለች።
ቀጥሎ ስለ ወታደራዊ ጥምረቱ ቁጥሮች ምን ይላሉ የሚለው ቀርቧል፦