ዓለማችን ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት 120 ቢሊዮን ዶላር መክሰሯ ተገለጸ
በ2022 በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት 120 ቢሊዮን ዶላር አጥታ ነበር
የመድህን ድርጅቶች ለአደጋዎች የከፈሉት ገንዘብ የ50 ቢሊዮን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል
ዓለማችን በስድስት ወራት ውስጥ በተፈጥሮ አደጋዎች 120 ቢሊዮን ዶላር ጉዳት እንደደረሰባት ተገለጸ።
የያዝነው 2023 ዓመት ከፍተኛ የተፈጥሮ አደጋዎች የተመዘገቡበት ዓመት መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል።
ተመድ በሪፖርቱ አክሎም ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት የደረሱ ጉዳቶች 123 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።
የአየር ንብረት ለውጥ እየፈተነው ያለው የሳመን አሳ የጅምላ ፍልሰት
የደረሰው ጉዳት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወራት ጋር ሲነጻጸር የሶስት ቢሊዮን ዶላር ጭማሪ እንዳሳየም ተገልጿል።
ይህ በዚህ እንዳለም የመድህን ድርጅቶች ለደረሱ የተፈጥሮ ጉዳቶች የከፈሉት ካሳ ክፍያ የ50 ቢሊዮን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል።
ባለፈው ዓመት ለደረሱ የተፈጥሮ አደጋዎች ከኢንሹራንስ ኩባንያዎች የተከፈለ ገንዘብ 48 ቢሊዮን ዶላር ነበር ተብሏል።
በቱርክ እና ሶሪያ የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች የ34 ቢሊዮን ዶላር ጉዳት ማድረሳቸው አይዘነጋም።
የመድህን ወይም ኢንሹራንስ ኩባንያዎች በቱርክ እና ሶሪያ ለደረሱ አደጋዎች 5 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ክፍያ መፈጸማቸው ተገልጿል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለደረሱ የተፈጥሮ አደጋዎች ካሳ ከከፈሉ የመድህን ድርጅቶች መካከል 70 በመቶዎቹ የአሜሪካ ተቋማት ናቸው ተብሏል።