የአየር ንብረት ለውጥ እየፈተነው ያለው የሳመን አሳ የጅምላ ፍልሰት
የሳመን አሳ የጅምላ ፍልሰት ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ኪሳራ እንዳለውም ተረጋግጧል
በፓስፊክ ውቅያኖስ በአሜሪካ የባህር ዳርቻዎች አሳ አጥማጆች መረባቸው ሲጥሉ ከሳመን ይልቅ ሌሎች ዝርያዎችን ማጥመዳቸው አስደንጋጭ ሆኗል
የአየር ንብረት ለውጥ አስከፊነት ጋር የማይፈለጉ የአሳ ዝርያዎችና ሌሎች ነፍሳቶች ክስተት እንዲጨምር አድርጓል።
በፓስፊክ ውቅያኖስ በአሜሪካ የባህር ዳርቻዎች አሳ አጥማጆች መረባቸው ሲጥሉ ከሳመን ይልቅ ሌሎች ዝርያዎችን ማጥመዳቸው አስደንጋጭ ሆኗል።
ይህም የተመራማሪዎች አይኖች ወደ ውቅያኖስ እንዲያዞሩ ያደረጋቸው ሲሆን፤ ምን እንደተፈጠረ ለመረዳት መረጃዎችን አሰባስበዋል።
በዚህም ተመራማሪዎቹ ለክስተቱ የአየር ንብረት ለውጥ የተደበቀ እጅ እንዳለው ተገንዝበዋል። አጥማጆች ኢላማ ያልሆኑ ዝርያዎችን በስህተት እየያዙ ነው ተብሏል።
በቅርብ ጊዜ የተደረገ ጥናት እንደሚያመለክተው ውቅያኖሶች ሞቃታማ በሆኑባቸው ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ያልተፈለጉ የባህር ነፍሳት መጠመድን ያስከትላል።
ተመራማሪዎቹ ከብሄራዊ የውቅያኖስና የከባቢ አየር አስተዳደር የተሰበሰቀ የ20 ዓመታት የውቅያኖስ የሙቀት ለውጥ መረጃዎችን ተንትነዋል።
የሳመን አሳዎች ከሙቀት ለማምለጥ ብዙውን ጊዜ ጥልቀት በሌለው አካባቢ ከባህር ወለል አጠገብ ይኖራሉ። ሌሎች የባህር ነፍሳት ደግሞ ከውኃው ወለል በታች ከ 200 እስከ 300 ሜትር ጥልቀት ላይ የሚኖሩ ሲሆን፤ እነዚህም በአሳ አጥማጆች የታለሙ ናቸው።
ተመራማሪዎቹ የሙቀት መጠኑ እየጨመረ ሲሄድ ሳመን ማምለጡን አስተውለዋል።
የጥናቱ አዘጋጆች በ2002 እና 2021 መካከል ከ67 ሽህ በላይ ሳመኖች በአሳ ማጥመጃ ውስጥ ተይዘዋል።
ሁነቱ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ኪሳራ እንዳለውም ተረጋግጧል። በሌላ በኩል ብዙ የሳመን አሳዎች ቁጥር እየቀነሰ በመምጣቱ የመጥፋት አደጋም ተጋርጦባቸዋል።