በሱዳን በትንሹ 220ሺ ሰዎች በጎርፍና በከባድ ዝናብ ተጠቅተዋል፡ ተመድ
እንደቃል አቀባዩ ከሆነ ተመድ ከአጋሮቹ ጋር በመሆን 1.6 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ መጠየቁን ገልጸዋል
ተመድ በሱዳን ከሚገኙ 18 ግዛቶች ውስጥ 17ቱ ውስጥ ከባድ ዝናብና ጎርፍ መከሰቱን ገልጿል
ተመድ በሱዳን ከሚገኙ 18 ግዛቶች ውስጥ 17ቱ ውስጥ ከባድ ዝናብና ጎርፍ መከሰቱን ገልጿል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ቃል አቀባይ እንዳስታወቁት በሱዳን ከሚገኙት 18 ግዛቶች ውስጥ በ17ቱ እየተከሰተ ባለው ከባድ ዝናብና ጎርፍ ምክንያት ወደ 220ሺ የሚጠጉ ሰዎች ህይወት አደጋ ላይ ወድቋል፡፡
“ከ20ሺ በላይ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፤ተጨማሪ 20ሺ ቤቶችም” እንዲሁ በጎርፍ ምክንያት መውደማቸውን የገለጹት የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ቃል አቀባይ የሆኑት ስቴፋኒ ዱጃሪክ ናቸው፡፡
ቃል አቀባዩ እንደገለጹት ከ2ሺ በላይ የውሃ ምንጮች ተበክለዋል፤ወይም ከአገልግሎት ውጭ በመሆናቸው የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስፈልገውን የንጹህ ውሃ አቅርቦት ጥያቄ ውስጥ አስግብቶታል፡፡
በሀምሌ ወር የቦት ዳም መደርመስ በ100ሺ ሰዎች የውሃ አቅርቦት ላይ ችግር ፈጥሯል ያሉት ቃል አቀባዩ መንግስትና የእርዳታ ድርጅቶች የፕላስቲክ ምንጣፎችንና፣ድንኳኖችን፣ መድኃኒት፣ የውሃ ማጣሪያ መሳሪያዎችንና የወባ መከላከያ አጎበሮችን እያከፋፈሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ለ250ሺ የሚሆን እርዳታን በፍጥነት ማዳረስ የተቻለው በተመድ ድርጅቶችና በአጋሮች ምክንያት መሆኑን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡
ነገርግን ቃል አቀባዩ እርዳታዎቹ እያላቁ ስለሆነ አስቸኳይ ለጋሽ ድርጅጾች ድጋፍ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡እንደቃል አቀባዩ ከሆነ ተመድ ከአጋሮቹ ጋር በመሆን 1.6 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ መጠያቸውን ገልጸዋል፡፡