በሱዳን በድንገት በተደረመሰ ግድብ ምክንያት 6 መቶ ቤቶች ፈረሱ
በሱዳን በድንገት በተደረመሰ ግድብ ምክንያት 6 መቶ ቤቶች ፈረሱ
በሱዳን በብሉ ናይል ግዛት በድንገት የተደረመሰ ግድብ 6 መቶ ቤቶችን ከጥቅም ውጭ ማድረጉም ሲጂቲኤን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃንን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
አምስት ቢሊዮን ኩቢክ ሜትር ውሃ ይዞ የነበረው ቦት የተሰኘው ግድብ ተደርምሶ በብሉ ናይል ግዛት ቦት ከተማ የሚገኙ 6 መቶ ቤቶችን መደርመሱን ዘገባው አመልክቷል፡፡
ውሃው ሌሎች 600 የሚሆኑ ቤተሰቦችን እንደከበበም ተገልጿል፡፡ ውሃው ከሶስት አቅጣጫ ስለሚመጣ የተከበቡትን ቤተሰቦች የማዳኑ ስራ እጅግ ፈታኝ ሆኗል፡፡ የአካባቢው ባለስልጣናት መፈናቀል ሊከሰት እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡ በየዓመቱ በሰኔና በሀምሌ ወቅት በሱዳን በከባድ ዝናብ ምክንያት ጎርፍ ይከሰታል፡፡
የሱዳን የሜትሮሎጂ ባለስልጣናት ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል ከመካከለኛ እስከ ከባድ ዝናብ እስከ እሁድ ድረስ ሊቀጥል እንደሚችል ባለፈው ሀሙስ አስጠንቅቀው ነበር፡፡