ወላይታ ዞን ወደ 'አዲሱ ክልል' ይካተት የሚለው አማራጭ አብላጫ ድምጽ ማግኘቱን ቦርዱ አስታወቀ
ምርጫ ቦርዱ በዞኑ ከተመዘገቡት 849 ሺ 896 መራጮች ውስጥ 849,896 መራጮች ድምጽ መስጠታቸውን ገልጿል

ምርጫ ቦርድ ጥር 29 በዞኑ የተካሄደውን ምርጫ ውጤት መሰረዙን መግለጹ ይታወሳል
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 12 በወላይታ ዞን የተካሄደውን ህዝበ ውሳኔ ጊዜያዊ ጠቅላላ ውጤት በዛሬው እለት ይፉ አድርጓል።
ወላይታ ዞን ከኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጌዲኦ እና ጎፋ እንዲሁም ከአምስት ልዩ ወረዳዎች ጋር በአንድ ክልል መደራጀትን "እደግፋለሁ" ወይም "አልደግፍም" የሚሉ አማራጮች ነበር የቀረቡት።
በውጤቱ መሰረት ዞኑ አዲስ ወደሚቋቋመው ክልል ይካተት የሚለው አማራጭ አብላጫ ድሞጽ አግኝቷል
ምርጫ ቦርዱ በዞኑ ከተመዘገቡት 849 ሺ 896 መራጮች ውስጥ 849,896 መራጮች ድምጽ መስጠታቸውን ገልጿል
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጥር 29 በተካሄደው ምርጫ፣ በምርጫ ጣቢያዎች ተካሂዷል ባለው ህገወጥ ተግባር የዞኑን ምርጫው ውጤት መሰረዙን መግለጹ ይታወሳል።
በወላይታ ከ1 ሽህ 112 የምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ 96 በመቶዎቹ መጠነ ሰፊ ጥሰት የተፈጸመባቸው ብሎ ነበር ቦርዱ።
ከወላይታ ዞን ውጭ ባሉ 10 አደረጃጀቶች የጸጥታ ችግር አለመታየቱን እና ወደ አዳሱ ክልል ለመካተት መወሰናቸውን ቦርዱ ውጤቱን ይፋ ባደረገበት ወቅት መግለጹ ይታወሳል።
ከ56 በላይ ብሔር ብሔረሰቦችን አቅፎ በነበረው በቀድሞው የደቡብ ክልል ውስጥ የነበሩ ዞኖች በተናጠል እና በጋራ የራሳቸውን ክልል በመመሰረት ላይ ናቸው።
በኢትዮጵያ 10ኛ ክልል ሆኖ የተመዘገው እና ሀዋሳን ዋና ከተማ አድርጎ የተቋቋመው የሲዳማ ዞን ቀዳሚ ነበር።
የሲዳማ ዞን ክልል መሆኑን ተከትሎ በወላይታ፣ በጉራጌ እና በሌሎች ዞኖች የክልል እንሁን ጥያቄዎች በስፋት ሲነሱ ቆይተዋል።
የበጀት እጥረት ያስከትላል በሚል ምክንያት ሁሉም ዞኖች ያቀረቡትን ወደ ክልል አወቃቀር እንሸጋገር ጥያቄ እንደማይቀበለው መንግስት ገልጿል።