የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ጥር 29 በደቡብ ክልል ያካሄደውን ህዝበ ውሳኔ ውጤት አቅርቧል
"በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል" ህዝበ ውሳኔ የወላይታ ዞን ውጤት ተሰረዘ።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ጥር 29 ያደረገውን ህዝበ ውሳኔ ሪፖርትና ውጤት ይፋ አድርጓል።
በኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ዎላይታ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎ ዞኖችና እና በቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ ልዩ ወረዳዎች የተካሄደው ህዝበ ውሳኔው "የጸጥታ ችግር አልታበትም" ተብሏል።
አምስቱም የቦርዱ አባላት በተገኙበት የተሰጠው መግለጫ፤ 900 ሽህ ድምጾች በጥሰት ምክንያት ተሰርዘዋል።
ተፈጽሟል ባለው የምርጫ ጥሰት ውጤት ማሳወቁን ያዘገየው ቦርዱ የወላይታን ውጤት ሰርዟል።
ቦርዱ ያጸደቀው ውጤት እንደሚያመለክተው 10ሩ አደረጃጀቶች በአዲሱ ክልል ለመደራጀት ይሁንታ ሰጥተዋል።
ወላይታ አንድ ሽህ 112 የምርጫ ጣቢያዎች ናሙና የተወሰደባቸው 96 በመቶዎቹ መጠነ ሰፊ ጥሰት የተፈጸመባቸው ሲሆን በሌሎቹ 10 አደረጃጀቶች ደግሞ 81 የምርጫ ጣቢያዎች ውጤት ተሰርዟል።
በዚህም የወላይታ ውጤት የተሰረዘ መሆኑን ያሳወቀው ቦርዱ፤ በዞኑ ምርጫው እንዲደገም ወስኗል።
አጠቃላይ የምርጫው ውጤት የወላይታ ድምጽ በመሰረዙ "ቁጥሩን በመቶኛ ልንጠቅስ አንችልም" በማለት የቦርዱ ሰብሳቢ ተናግረዋል።
ውጤት በተሰረዘባቸው ሌሎች አካባቢዎች የምርጫውን ውጤት ስለማይቀር በድጋሚ ምርጫው እንደማይደረግ ታውቋል።
የወላይታ ህዘዝበ ውሳኔ አጠቃላይ የምርጫ ሂደቱ ተአማኒነት ያሳጣና የምርጫ ውጤቱም የሚያዛባ ሆኖ በመገኘቱ በድጋሚ እንዲደረግ ተወስኗል።
የወላይታን ህዝበ ውሳኔ ዳግም ለማድረግ የበጀት ጥያቄ አለማቅረቡን ሰብሳቢዋ ብርቱካን ሚዴቅሳ ተናግረዋል።