ፖለቲካ
ሩሲያ፣ ኘሬዝደንት ማክሮን በብሪክስ ስብሰባ እንዲካፈሉ እንደማትፈልግ ገለጸች
ሩሲያ ይህን ያለችው የፈረንሳዩ ፕሬዝጀንት ማክሮን በደቡብ አፍሪካው የብሪክስ ስብሰባ ለመካፈል ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ ነው
ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ፈረንሳይን ጨምሮ ከምዕራባውያን ሀገራት ጋር ያላት ግንኙነት ሻክሯል
ሩሲያ ፕሬዝደንት ማክሮን ደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው የብሪክስ ስብሰባ ለመካፈል መጠየቃቸውን ተቃወመች።
ሩሲያ ይህን ያለችው የፈረንሳዩ ፕሬዝጀንት ማክሮን በደቡብ አፍሪካው የብሪክስ ስብሰባ ለመካፈል ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ ነው።
የሩሲያ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ርያብኮቭ እንደተናገሩት ፈረንሳይ በሩሲያ ላይ የያዘችው አቋም ሲታይ የኘሬዝደንቱ መሳተፍ ተገቢ አይሆንም ብለዋል።
"ስለጉዳዩ ለደቡብ አፍሪካ ጋዶቻችን ተናግረናል። የአኛ ስጋት ሙሉ በሙሉ ከግምት ይገባል ብለን እንጠብቃለን" ብለዋል ርይያብኮቭ።
ርያብኮቭ ደቡብ አፍሪካ የስብሰባው አዘጋጁ ስለሆነች ማክሮንን መጋበዝ ብትችልም፣ ሌሎቹን የብሪክስ አባላትን ማማከር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ፈረንሳይን ጨምሮ ከምዕራባውያን ሀገራት ጋር ያላት ግንኙነት ሻክሯል።