ጠቅላይ ሚኒስትር ኒታንያሁ አሁንም መንግስት መመስረት የሚያስችል አብላጫ ድምጽ አላገኙም
ኒታንያሁ አሁንም መንግስት መመስረት የሚያስችል አብላጫ ድምጽ አላገኙም
የእስራኤልን ምርጫ እየመሩ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኒታንያሁ አሁንም መንግስት መመስረት የሚያስችል አብላጫ ድምጽ አለማግኘታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በእስራኤል በአንድ አመት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ በትናንትናው እለት በተካሄደው ምርጫ ኒታንያሁ መንግስት መመስረት የሚያስችል ድምጽ አለማግኘታቸውን መራጮች ከምርጫ በኋላ የሰጡት አስተያየት እንደሚያሳይ ተነግሯል፡፡
በሶስት የእስራኤል ዋና ዋና የቴሌቪዥን ማሰራጫ ጣቢያዎች ቅድመ ትንበያ መሰረት የቀኝ ዘመም ፓርቲ መሪ የሆኑት ኒታንያሁ ዋና ተቀናቃኛቸው የሆኑትን የቀድሞውን የጦር ኃይል ዋና አዛዥ ቤኒ ጋንዝን ማሸነፋቸውን አስታውቀዋል፡፡
ቤኒ ጋንዘ ለዘብተኛ የሚባለው የ“ብሉ ኤንድ ኋይት ፓርቲ” መሪ ናቸው፡፡
በቅርብ በወጣው የመራጮች አስያየት ደግሞ ኒታንያሁ አብላጫ የፓርላማ ወንበር ለማግኘት ሁለት መቀመጫ እንዳነሳቸው የታወቀ ሲሆን ይህም ሌላ ችግር ሊኖር እንደሚችል የሚያመላክት ነው ተብሏል፡፡