ኢኮኖሚ
የተሽከርካሪውን ጥንካሬ ለማሳየት ያልተለመደ ነገር ያደረገው ኩባንያ
የቻይናው ቼሪ የተሽከርካሪ አምራች ድርጅት አዲስ የገበያ ማስታወቂያ ይዞ ብቅ ብሏል
ድርጅቱ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎቹ በጥንካሬያቸው ወደር የላቸውም ብሏል
የተሽከርካሪውን ጥንካሬ ለማሳየት ያልተለመደ ነገር ያደረገው ኩባንያ
የተሽከርካሪ ምርቶች በየዘመኑ እየዘመኑ የመጡ ሲሆን አሁን ደግሞ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ምርቶች ተወዳጅ ምርቶች ሆነዋል፡፡
ከነዳጅ መወደድ እና አየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ተመራጭነታቸው እየጨመረ የመጣው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ዋነኛ
የአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ መፎካከሪያም ሆነዋል፡፡
በተለይም የቻይና አውቶሞቲቭ ኢንዱሰትሪዎች ከሀገራቸው አልፈው በመላው ዓለም ገበያን ለመቆጣጠር ፉክክር ውስጥ ሲሆኑ ቼሪ
የተሰኘው ኩባንያ ደንበኞቹን ለመሳብ አዲስ ማስታወቂያ ይዞ ብቅ ብሏል፡፡
የዚህ ኩባንያ ምርት የሖኑ ተሽከርካሪዎች በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ከመሆናቸው ባለፈ በጥንካሬያቸው ወደር ይላቸውም ብሏል፡፡
ድርጅቱ ኢኪው7 የተሰኘ የተሽከርካሪ ምርቱን ጥንካሬ ለማሳየት ሲል የተጠቀመው ምስል የብዙዎችን ትኩረት ስቧል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
በአንድ ጊዜ ቻርጀር እስከ 500 ኪሎ ሜትር እንደሚጓዝ የተገለጸው ይህ አዲስ ስሪት ተሽከርካሪ ሰባት ተሽከርካሪዎችን ባንድ ላይ ደራርቦ ማቆሙን አስታውቋል፡፡
የአንድ ተሽከርካሪ ጥንካሬ ጥሩ መሆኑ የሚለካው የራሱን ክብደት አራት እጥፍ በራሱ ላይ መጫን ሲችል ነው እንደሆነ የአውቶሞቲቭ ባለሙያዎች ይናገራሉ የተባለ ሲሆን ድርጅቱ ግን ሰባት ተሽከርካሪዎች ደራርቦ ለደንበኞቹ አሳይቷል፡፡
የአውሮፓው ቮልቮ ኩባንያ በዓለም የተሽከርካሪ ጥንካሬ ቀዳሚ እንደነበረ ሲገለጽ አሁን ደግሞ ቼሪ የተሰኘው የቻይናው የተሽከርካሪ ኩባንያ በጥንካሬ ቀዳሚ ነኝ ብሏል፡፡
ከባድ ተሽከርካሪዎችን በማምረት የሚታወቀው ቮልቮ ኩባንያ አሁን ላይ በቻይናው ጂሊ የተገዛ ሲሆን የምርቶቹን ጥንካሬ ማስተዋወቅ ዋነኛ የገበያ ስልቱም ነበር፡፡