በሱዳን ግጭት ወደ አንድ ሽህ የሚጠጉ ሰዎች መገደላቸው ተነገረ
ካርቱም አዲስ የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ ከመሆኑ ከሰዓታት በፊት መረጋጋት እንደታየባት ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ከፈረንጆቹ ሚያዝያ 15 ጀምሮ በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መካከል በተደረገው ጦርነት ወደ አንድ ሽህ የሚጠጉ ሰዎች ተገድለዋል።
የአናዶሉ ዘጋቢ እሁድ ምሽት ማዕከላዊ ካርቱም፣ ሰሜን ባህር አካባቢ እና ኦምዱርማንን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ከባድ ግጭቶች ተሰምተዋል ብሏል።
እሁድ እለት ሳዑዲ አረቢያ እና አሜሪካ ከሰኞ ምሽት ጀምሮ በሱዳን ተቀናቃኝ ቡድኖች ለ ሰባት ቀናት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት መድረሳቸውን አስታውቀዋል።
ሳዑዲ አረቢያ የጂዳ ውይይት ዘላቂ የሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት እና ግጭትን በውይይት ለመፍታት በማቀድ እንደሚቀጥል ገልጻለች።
በጦር ኃይሉ እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል ለሀገሪቱ የፖለቲካ ሽግግር ቁልፍ በሆነው የመከላከያ ውህደት ላይ አለመግባባት ተፈጥሮ ወደ ጦርነት አምርቷል።
ወታደራዊው ኃይሉ የጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሀምዶክን የሽግግር መንግስት ካሰናበተ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካወጀ በኋላ በፖለቲካ ኃይሎች እርምጃው “መፈንቅለ መንግስት” ሲሉ ፈርጀውታል።
በነሀሴ 2019 የጀመረው የሱዳን የሽግግር ጊዜ ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ በ2024 መጀመሪያ ላይ ምርጫ ይደረጋል የሚል ውጥን ነበር።