የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ተኩስ ለማቆም ተስማሙ
የቀድሞው ፕሬዝደንት አልበሽር በህዝባዊ አመጽ ከስልጣን መነሳታቸውን ተከትሎ ሀገሪቱ የማያባራ ቀውስ ውጥስ ገብታለች
የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ብሊንከን ተፋላሚ ኃይሎቹ እንዲያከብሩ ጠይቀዋል
የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ለሰባት ቀናት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት ተፈራርመዋል።
- የሱዳን ጦርነት በኢትዮጵያ ላይ የደቀናቸው ስጋቶች ምንድናቸው?
- አሜሪካ እና አጋሮቿ የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ለደረሱት 'ተኩስ አቁም ስምምነት' ተገዥ እንዲሆኑ እየሰሩ መሆኑን ገለጹ
ሀገሪቱን ቀውስ ውስጥ ያስገባት እና ከሚሊዮን በላይ ሱዳናውያን ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት የሆነው ግጭት ስድስተኛ ሳምንቱን ሲይዝ ተፋላሚዎች በትናንትናው እለት ተኩስ ለማቆም መስማማታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
አደራዳሪዎቹ አሜሪካ እና ሳኡዲ አረቢያ ባወጡት የጋራ መግለጫ ተኩስ አቁም ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል።
ሁለቱ ኃይሎች ከዚህ በፊት የደረሷቸው በርካታ የተኩስ አቁም ስምምነቶች ተግባራዊ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
ነገርግን ይህ ተኩክ አቁም በአሜሪካና በሳኡዲ አረቢያ የሚፈጸም እና በአለም አቀፍ የሞኒተሪንግ ዘዴ የሚደገፍ ነው ተብሏል።
ስምምነቱ ተፋላሚ ኃይሎቹ የሰብአዊ እርዳታ እንዲሰራጭ፣ መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲመለሱ እና ወታደሮች ከሆስፒታሎች እና ከህዝብ መገልገያ ማዕከላት እንዲወጡ የሚጠይቅ ነው።
የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ብሊንከን ተፋላሚ ኃይሎቹ እንዲያከብሩ ጠይቀዋል።
በጦርነቱን ተከትሎ በተፈጠረው አለመረጋጋት የምግብ እና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮች አቅርቦት መጠን እያሽቆለቆለ ነው።
የቀድሞው ፕሬዝደንት አልበሽር በህዝባዊ አመጽ ከስልጣን መነሳቱን ተከትሎ ሀገሪቱ የማያባራ ቀውስ ውጥስ ገብታለች።
በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት ሀገሪቱ ወደ ሲቪል አስተዳደር ለመሸጋገር የምታደርገውን ጥረት አደናቅፏል።