ኪቭ የሩሲያ ኃይሎች የተማረኩ የዩክሬን ወደታሮችን ገድለዋል ስትል ከሰሰች
ቪዲዮው፣ ወታደሮቹ ከተኙ በኋላ የሩሲያ የሚመስሉ ወታደሮች ሲተኩሱባቸው ከሳየ በኋላ ወዲያው ያበቃል
21 ወራት ባስቆጠረው የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት፣ ሩሲያ የጦር ወንጀል አልፈጸምኩም ስትል ታስተባብላለች
ኪቭ የሩሲያ ኃይሎች የተማረኩ የዩክሬን ወደታሮችን ገድለዋል ስትል ከሰሰች
ከተደበቁበት ወጥተው እጅ የሰጡ ሁለት የዩክሬን ወታደሮች ሲገደሉ የሚያሳይ ያልተረጋገጠ ቪዲዮ ከተለቀቀ በኋላ የኪቭ ባለስልጣናት ሞስኮን የጦር ወንጀል በመፈጸም ከሰዋል።
ይህ ያልተረጋገጠ ቪዲዮ አንድ ወታደር ከተደበቀበት እጁን ወደላይ አድርጎ ከወጣ በኋላ መሬት ሲወድቅ ታይቷል። ሁለተኛው ወታደርም በተመሳሳይ እጅ ወደ ላይ አደርጎ መሬት ላይ ተኝቷል።
ቪዲዮው፣ ወታደሮቹ ከተኙ በኋላ የሩሲያ የሚመስሉ ወታደሮች ሲተኩሱባቸው ከሳየ በኋላ ወዲያው ያበቃል።
የዩክሬኑ ጀነራል "ቪዲዮ የሩሲያን ዩኒፎርም የለበሱ ወታደሮች የዩክሬን ጦር ዩኒፎርምን በለበሱ ሁለት ያልታጠቁ ወታደሮችን ሲተኩሱባቸው ያሳያል" ብለዋል።
ሮይተርስ የቪዲዮውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ እንዳልቻለ ገልጿል።
21 ወራት ባስቆጠረው የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት፣ ሩሲያ የጦር ወንጀል አልፈጸምኩም ስትል ታስተባብላለች። ነገርግን ካቭ ሩሲያ የጦርነት ህግ ትጥሳለች የሚል ተደጋጋሚ ክስ አቅርባለች።
የተማረኩ ወታደሮችን መግደል የጦር ወንጀል መሆኑን የገለጸው የዩክሬን እንባ ጠባቂ ተቋም ሩሲያ የጄኔቫ ኮንቬንሽንን ጥሳለች፣ ለአለም አቀፍ ህግም ንቀቷን አሳይታለች ብሏል።
ቪዲዮውን ፖስት ያደረገው ዲፕስቴት የተሰኘው ታዋቂው የዩክሬን የጦር ጸኃፊ ቨዲዮው የተቀረጸው በዶኔስክ ግዛት በሚገኘው አቪድቪካ ግንባር መሆኑን ገልጿል።