ሩሲያ የወታደሮቿን ብዛት ወደ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ከፍ አደረገች
ፕሬዝዳንት ፑቲን ተጨማሪ 170 ሺህ ወታደሮች እንዲመለመሉ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ተብሏል
ሩሲያ በተያዘው ዓመት ብቻ 450 ሺህ አዲስ ወታደሮችን መመልመሏ ተገልጿል
ሩሲያ የወታደሮቿን ብዛት ወደ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ከፍ አደረገች፡፡
በዩክሬን ምድር ከምዕራባዊያን ጋር እየተዋጋች መሆኗን የምትገልጸው ሩሲያ የወታደሮቿን ቁጥር ወደ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ከፍ ለማድረግ መወሰኗ ተገልጿል፡፡
የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተጨማሪ 170 ሺህ ወታደሮች እንዲመለመሉ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ ፕሬዝዳንቱ አዲስ ወታደሮች ምልመላ እንዲደረግ የወሰኑት ሩሲያ የደህንነት ስጋት ስላለባት ነው፡፡
የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶ አዳዲስ አባላትን በመመልመል ላይ መሆኑ እና ወደ ሩሲያ የበለጠ መጠጋቱ ሞስኮ ተጨማሪ ወታደሮችን እንድትመለምል ማድረጉ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም በዩክሬን እየተደረገ ያለው ጦርነት እልባት አለማግኘቱ እና ምዕራባዊያን አሁንም በሩሲያ ላይ ደህንነት ሊደቅኑ የሚችሉ የጦር መሳሪያዎችን በድጋፍ መልክ በመስጠት ላይ መሆናቸው በሞስኮ ላይ የደህንነት ስጋት ደቅኗል ተብሏል፡፡
ሩሲያ የፈረንጆቹ 2023 ከገባ በኋላ ብቻ 452 ሺህ አዲስ ወታደሮችን የመለመለች ሲሆን ይህም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ሀገሪቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደር ቅጥር እንድትፈጽም ማድረጉ ተገልጿል፡፡
የሩሲያ ጦር የዩክሬኗን ከተማ እየከበበ መሆኑን የከተማዋ ባለስልጣናት ተናገሩ
ለሁለት ሳምንት በሚል የተጀመረው የዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት ሁለት ዓመት ሊሞላው ሶት ወራት ብቻ ቀርተውታል፡፡
ከሁለት ወር በፊት የተጀመረው የእስራኤል-ሀማስ ጦርነት የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት እንዲረሳ አድርጓል የተባለ ሲሆን ይህም ዩክሬንን እንዳሳሰባት ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ከሰሞኑ ተናግረዋል፡፡
ዓለም ሁሉ ዩክሬንን እንዳይረሳ ማድረግ አለብን ያሉት ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ምዕራባዊያን ለኪቭ ተጨማሪ የጦር መሳሪያ እንዲሰጡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡