የጸጥታው ምክርቤት ወደ ለሶማሊያ መንግስት የጦር መሳሪያ እንዳይተላለፍ የተጣለውን እገዳ ከ30 ባለፈው አርብ እለት አንስቶታል
በሶማሊያ ላይ ተጥሎ የነበረው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ከ30 አመታት በኋላ ተነሳ።
የተመድ የጸጥታው ምክርቤት ወደ ለሶማሊያ መንግስት እና የጸጥታ ሀይሎቿ የጦር መሳሪያ እንዳይተላለፍ የተጣለውን እገዳ ከ30 አመታት በኋላ ባለፈው አርብ እለት አንስቶታል።
የጸጥታው ም/ቤት በፈረንጆቹ 1992 በሶሚሊያ ላይ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ የጣለው፣ የሀገሪቱን መሪ መሀመድ ሲያድ ባሬን ያስወገዱት ተቀናቃኝ ታጣቂዎች መሳሪያ እንዳይደርሳቸው ለማድረግ ነው።
15 አባላት ያሉት የጸጥታው ምክርቤት በእንግሊዝ የቀረቡለትን ሁለት የውሳኔ ሀሳቦች አጽድቋል። በሶማሊያ ላይ ተጥሎ የነበረው ሁሉም አይነት የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንዲነሳ እና በአል ሸባብ ላይ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንዲጣል የሚሉ የውሳኔ ሀሳቦች ነበር በእኔግሊዝ የቀረቡት።
በሶማሊያ መንግስት ላይ ምንም አይነት የጦር መሳሪያ ማዕቀብ መኖር እንደሌለበት አንደኛው ረቂቅ የውሳኔ ተጠቅሷል።
በሀገሪቱ ባለው ደህንነቱ የተጠበቀ የመሳሪያ ማከማቻ ቦታ ቁጥር ስጋቱን የገለጸው የውሳኔ ሀሳቡ ግንባታ እንዲደረግ እና ሌሎች ሀገራት እርዳታ እንዲያደርጉ ጠይቋል።
ሶማሊያን በእስላማዊ የሼሪየአ ህግ ለማስተዳደር የሚፈልገው አልሸባብ ከፈንጆቹ 2006 ጀምሮ ደምአፋሳሽ ግጭት ውስጥ ከቷታል።
የሶማሊያ መንግስት ማዕቀቡ እንዲነሳለት ለረጅም ጊዜ ሲጠይቅ ቆይቷል።የጸጥታው ም/ቤትም ከ2013 ጀምሮ ነበር ማዕቀቡን በከፊል ማንሳት የጀመረው።
የሶማሊያ ፕሬዝደንት ሀሰን ሼህ መሀመድ ባለፈው ሳምንት እንደተናገሩት ሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ከሚወጣበት በፊት አልሸባብን ለማጥፋት አንድ አመት ብቻ ነው የቀራት ሲሉተናግረዋል።