ከ36 ዓመት በፊት ከእስራኤል ግድያ ያመለጡት ካሊድ ማሻል ሐማስን በጊዜያዊነት መምራት ጀመሩ
ካሊድ ማሻል ከሐማስ መስራቾች አንዱ ሲሆኑ በቱርክ ይኖራሉ
ለያህያ ሲንዋር ግድያ ሐማስ እስራኤል ይበቀላል ሲሉ ዝተዋል
ከ36 ዓመት በፊት ከእስራኤል ግድያ ያመለጡት ካሊድ ማሻል ሐማስን በጊዜያዊነት መምራት ጀመሩ፡፡
ለፍልስጤም ነጻነት እታገላለሁ የሚለው ሐማስ ከአንድ ዓመት በፊት በእስራኤል ላይ ልተጠበቀ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ጦርነት አድማሱን እያሰፋ ይገኛል፡፡
የዚህ ጥቃት ዋነኛ አቀናባሪ የሚባሉት ያህያ ሲንዋር ከሶት ሳምንት በፊት በእስራኤል ጦር በጋዛ መገደላቸው ይታወሳል፡፡
ይህን ተከትሎ ሐማስ ከድርጅቱ መስራቾች ውስጥ አንዱ የሆኑት ካሊድ ማሻልን በጊዜያዊነት የድርጅቱ የፖለቲካ ቢሮ ሀላፊ ሆነዋል፡፡
ሐማስ በተመሰረተ በዓመቱ በእስራኤል የስለላ ድርጅት ባለሙያዎች አማካኝነት ከግድያ ለጥቂት የተረፉት ማሻል በዌስት ባንክ ነበር የተወለዱት፡፡
የፊዚክስ መምህር የሆኑት ካሊድ ማሻል ሐማስን ከመመስረታቸው በተጨማሪ ከፈረንጆቹ 1996 እስከ 2017 ድረስ የሐማስ የፖለቲካ ቢሮ ሀላፊ ሆነው አገልግለዋል፡፡
በእስራኤል የተገደለው የሐማስ መሪ ያህያ ሲንዋር ማን ነው?
በወቅቱ ከሶስት ሳምንት በፊት በተገደሉት ያህያ ሲንዋር ተተክተው የነበሩት ካሊድ ማሻል አሁን ደግሞ አጋራቸው ሲንዋርን ተክተው የሀማስ ጊዜያዊ መሪ ሆነው መመረጣቸው ተገልጿል፡፡
በቱርክ ኢስታምቡል እንደሚኖሩ የተገለጸው ማሻል በያህያ ሲንዋር መታሰቢያ ፕሮግራም ላይ ባደረጉት ንግግር ሐማስ እስራኤልን ይበቀላል ሲሉ መዛታቸውን ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡
“ለሲንዋር መታሰቢያ በእስራኤል ላይ የጥቃት ወጀብ እናዘንባለን” ያሉት ማሻል በሐማስ የፖለቲካ እንቅስቀሴ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጋዛ ውጪ የሚኖር መሪ ሆነዋል፡፡