“አፕል”ን ጨምሮ ሌሎች ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን የገበያ ኃይል ለመቆጣጠር እንደሚፈልጉ መረጃዎች ይጠቁማሉ
የአሜሪካ ሰኔት የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በቀላሉ ውህደት እንዳይፈጥሩ የሚገድብ ረቂቅ ህግ ይፋ አደረገ፡፡
ረቂቅ ህጉን ለሰኔት ያቀረቡት ሁለት የአሜሪካ ሴነተሮች ሲሆኑ ህጉን ያስፈለገበት ምክንያት አማዞን ከሌሎች የቴክኖሎጂ ግዙፍ ኩባንያዎች የሚያደርገውን ውህደት ለመገደብ ነው ተብለዋል፡፡
በዲሞክራት ፅ/ቤት የመገኘውን የሴኔቱ የዳኝነት ኮሚቴ የጸረ እምነት ቡድን መሪ ሴኔተር ኤሚ ክሎቡቻር የአሁኑ ረቂቅ ህግ መንግስት የጸረ እምነት ህግን ይጥሳል ብሎ የሚያምንባቸውን ስምምነቶች፣ድርጅቶቹ ለዳኛ እንዲያረጋግጡ በማድረግ ስምምነቱ ለውድድር ጥሩ እና ህጋዊ መሆናቸው ለማረጋገጥ የሚያስችል እንደሆነ አስረድቷል።
“እኔ እና የሪፐብሊካኑ ቶም ኮተን ቀደም ሲል እንደ አልፋቤት ጎግል እና ፌስቡክ ባሉ ኩባንያዎች ላይ ያነጣጠረ ህግ አውጥተን ነበር” የሚሉት ሰኔተሯ አሁን ላይ ኩባንያዎች ከመወዳደር ይልቅ ተቀናቃኞቻቸውን ለመግዛት ሲመርጡ እንደሚስተዋልም አንስቷል፡፡
ሴነተር ክሎቡቻር “ይህ የሁለትዮሽ ህግ ለዋና ዲጂታል ማእቀፎች ተፎካካሪዎቻቸውን ለማስወገድ እና የገበያ ኃይል ለማጎልበት አስቸጋሪ በማድረግ እነዚያን ህገ ወጥነትን ያቆማል"ም ብሏል፡፡
የዲሞክራቲክ ተወካይ ሃኪም ጄፍሪስ እና ሌሎችም የቀረበው ተመሳሳይ ረቂቅ ህግ በተወካዮች ምክር ቤት የዳኝነት ኮሚቴ ጸድቆ በሙሉ ምክር ቤት ድምጽ እንዲጸድቅ በሴነቱ ጠረጴዛ ላይ መሆም ተገልጸዋል።
እንደ አፕል ያሉ የኢንዱስትሪ መሪ ኩባንያዎችን ጨምሮ ሌሎች ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን የገበያ ኃይል ለመቆጣጠር እንደሚፈልጉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡