
ኡጋንዳ ብሪክስን የተቀላቀለች ሶስተኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ትሆናለች
የብሪክስ አባል ይሆናሉ የተባሉ ሀገራት እነማን ናቸው?
ከ15 ዓመያት በፊት በብራዚል ፣ ሩሲያ፣ ሕንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ የተመሰረተው ብሪክስ በየጊዜው አዳዲስ ሀገራትን በአባልነት ይቀበላል።
ከአንድ ዓመት በፊት ኢትዮጵያን ጨምሮ ግብጽ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬት፣ ሳውዲ አረቢያ እና ኢራንን በአባልነት መቀበሉ ይታወሳል።
ከጥቂት ቀናት በኋላ በሚጀመረው በፈረንጆቹ 2025 ጀምሮም አባል ለመሆን ካቀረቡ ሀገራት መካከል የተወሰኑ ሀገራትን በአባልነት እንደሚቀበል አስታውቋል።
አባል ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁ ሀገራት መካከልም ኡጋንዳ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ማሌዥያ፣ ታይላንድ፣ ቤላሩስ፣ቦሊቪያ እና ኩባ ዋነኞቹ ናቸው
ተብሏል