ዘለንስኪ በብሪክስ ጉባኤ ተሳትፎ ምክንያት የተመድን ዋና ጸኃፊ የኪቭ ጉብኝት እቅድ ውድቅ አደረጉ
ኪቭ በሩሲያ በተካሄደው ስብስብ ላይ የጉተሬዝ መገኘት እና የጉባኤው አዘጋጅ ከሆኑት የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ሰላምታ መለዋወጣቸው አበሳጭቷታል።
የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ሰኞ እለት ጉተሬዝ የብሪክስን ጉባኤ እንዲሳተፉ የቀረበላቸውን ግብዣ መቀበላቸው የተመድን ዝና የሚጎዳ ነው ብሏል
ዘለንስኪ በብሪክስ ጉባኤ ተሳትፎ ምክንያት የተመድን ዋና ጸኃፊ የኪቭ ጉብኝት እቅድ ውድቅ አደረጉ።
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በዚህ ሳምንት በሩሲያ በተካሄደው የብሪክስ ጉባኤ ላይ በመሳተፋቸው ምክንያት ኪቭን ለመጎብኘት የያዙትን እቅድ ውድቅ እንዳደረጉባቸው የዩክሬን ባለስልጣን ተናግረዋል።
ኪቭ ባለፈው ሀሙስ በሩሲያዋ ካዛን ከተማ በተካሄደው ስብስብ ላይ የጉተሬዝ መገኘት እና የጉባኤው አዘጋጅ ከሆኑት የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ሰላምታ መለዋወጣቸው አበሳጭቷታል።
የተመድ ምክትል ቃል አቀይ ፋርሃን ሀቅ በብሪክስ ገባኤ ሰላም እንዲመጣ ጥሪ ያቀረቡት ጉተሬዝ ባለፈው መስከረም ወር በኒው ዮርክ ከዘለንስኪ ጋር በተገናኙበት ወቅት በዩክሬን ስለሚያደርጉት ጉብኝት ተወያይተው ነበር ብለዋል።
ሀቅ አክለውም እንደገለጹት ከእዚያ ጊዜ ጀምሮ ተመድ እና ዩክሬን ጉብኝቱ የሚያካሄድበትን ለሁለቱም ምቹ የሆነ ጊዜ የመምረጥ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። ነገርግን እስካሀኑን የተወሰነ ጊዜ የለም ብለዋል ቃል አቀባዩ።
አሁን ላይ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ጉተሬዝ በብሪክስ ጉባኤ በመሳተፋቸው ምክንያት ጉብኝቱን መሰረዛቸውን ሮይተርስ አንድ ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ የዩክሬን ባለስልጣንን ጠቅሶ ዘግቧል።
የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ሰኞ እለት ጉተሬዝ የብሪክስን ጉባኤ እንዲሳተፉ የቀረበላቸውን ግብዣ መቀበላቸው የተመድን ዝና የሚጎዳ ነው ብሏል። ዘለንስኪ የጉተሬዝን መሳተፍ አውግዘዋል።
"ምንም እንኳን የተወሰኑ ባለስልጣናት የካዛንን ስብሰባ ከተመድ ቻርተር ቢያስበልጡም፣ አለም የሀገራት መብት እና አለምአቀፍ ህግ መከበር አለበት በሚለው መርህ ላይ እንደጸና ነው" ብለዋል ዘለንስኪ።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ በፈጸመችው "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ"በሽዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ በሚሊዮኖች ደግሞ ተሰደዋል። ባለፈው ሀሙስ በሩሲያ የተካሄደው የብሪክስ ስብሰባ አላማው ምዕራባውያን ያልሆኑ ሀገራትን አቅም ለማሳየት ነው።